የዶሮ እርባታ ፓኬጅ

Uncategorized
Spread the love

የኢትዮጵያ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

1.  መግቢያ

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዶሮ ሀብት ባላቤት ስትሆን እንደ ማዕከላዊ መረጃ አገልግሎት 2013 ዓ/ም  መሠረት ሀገራችን አጠቃላይ የዶሮ ቁጠር ብዛት 57 ሚሊዮን  ሲሆን ከዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የሀገረሰብ  የዶሮ ዝርያ 78.85 በመቶ ሲሆን የተዳቀሉ 12.02 በመቶ እና የተሸሻሉ የዉጪ ዝርያዎች 9.11% ድርሻ ይይዛሉ። አጠቃላይ ዓመታዊ የእንቁላል ምርት 369 ሚሊዮን ሲሆን ምንም እንኳን አብላጫውን የዶሮ ቁጥር የሀገር በቀል ዶሮ ዝርያዎች የያዘ ቢሆንም ዓመታዊ የእንቁላል ምርታቸዉ ግን 33.5% ድርሻ ብቻ ነው ፡፡ነገር ግን አነስተኛ ቁጥር ያለቸው የተዳቀሉናየተሸሻሉ የዉጪ ዝርያዎች ከአመታዊ  የእንቁላል ምርት 65.5% ከፍተኛው ድርሻ ይይዛሉ። በተመሳሳይም የዶሮ ስጋ ምርት ከህዝቡ ስጋ ፍጆታ  ጋር ሲነፃፀር በጣም ያነሰ ነው  እንደ ግብርና ሚኒስተር  (2014) አመታዊ ሪፖርት መረጃ መሠረት 90 ሺህ ቶን የዶሮ ሥጋ ምርት እነደምመረት መረጃው ያሳያል ከአጠቃላይ የዶሮ ስጋ ምርት 17 % ሺህ ቶን ከሀገርሰብ ዶሮ የተገኘ ሲሆን ቀሪው  ምርት ግን ከተዳቀሉ እና ከተሻሻሉ የዉጪ ዝርያዎች የተገኘ ነው።በሌላ በኩል በተለይ ከፕሮቲን እጥረት በመነጨ የህጻናት ሞት ፤ መቀጨጭ ፤ እንዲሁም የበሽታ መስፋፋት በሰፊው የሚታዩ ናቸው፡፡ ከሌሎች ዘርፎች ሲወዳደር የዶሮ እርባታ ትኩረት ከተሰጠው ይህንን ችግር በቀላሉና አጠር ባለ ጊዜ መቋቋም ያስችላል፡፡

የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ አንጻራዊ የገቢ ዕድገት መኖሩ፣ የከተሞች መስፋፋት እና የአኗኗር ዘይቤ በመለወጥ ምክንያት የዶሮ ምርት ፍላጎት እየጨመረ ነው። ይሁን እንጂ አገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዶሮ ምርቶች (እንቁላል እና የዶሮ ሥጋ) ከአገር ውስጥ ምርቶች ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉ ከሌሎች አጎራባች ሀገራት ጋር የዶሮ ምርት ሲነጻጸር   በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ  የኢትዮጵያ እንቁላል እና የዶሮ ስጋ ፍጆታ ከብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ሲነጻጸር ከ2-10 እጥፍ ያነሰ መሆኑን መረጃዎች ያማላክታሉ።  እንደ ማከላዊ መረጃ አገልግሎት የ2012/13 መረጃ መሠረት የሀገሪቱ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ  እንቁላል ፍጆታ 0.07 ኪ.ግ አይበልጥም የዶሮ ስጋ ፍጆታ ደግሞ 0.6 ኪ.ግ በሰው ነዉ፡፡

ለዶሮ ሀብት ልማት አለመስፋፋትና ምርት ማነስ ዋነኞቹ ችግሮች የዶሮ ተላላፊ በሽታዎች በቁጥጥር ስር አለመዋል ፤ የሀገር በቀል  ዝርያ ምርታማ አለመሆንና ምርታማ የሆኑ የዉጪ ዝርያ በበቂ ሁኔታ አለማቅረብ/እጥረት ፤ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የመኖ እጥረት ፤ የኤክስቴንሽንና የምርምር አገልግሎቶች ትስስር አለመጠናከር ፤ በሙያው የሰለጠነ የሰው ኃይል አናሳነት ፤ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ውስንነት ፤ የገበያ ትስስር ስርዓት አለመዘርጋት ፤ የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ ውስን መሆንና ተገቢውን ትኩረት ለልማቱ አለመስጠቱ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ አስፈላጊው ጥረት የተደረገ ሲሆን ከነዚህ ጥረቶችም አንዱ የሆነው ለተለያዩ የቴክኖሎጂ ደረጃዎች አማራጭ ፓኬጆችን ማዘጋጀትና በአተገባበሩ ላይ ስልጠና መስጠት አንዱ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ወቅቱንና ቴክኖሎጂው የሚጠይቀውን አማራጭ ፓኬጆችን መከለስ በተለይም ባለሀብቱና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጎላ ተሳትፎ እንዲያደርጉና ሀገሪቷ ለነደፈችው የ10 ዓመት መሪ እቅድ እና  የሌማት ቱሩፋት  አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን የኤክስቴንሽን ድጋፍ ማድረግ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በዚህ መሰረት ይህንን የስጋ፣ የዕንቁላል ዶሮ እርባታ ፤የቄብ ማምረት እነዲሁም የተሸሻለ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ ሀገሪቷ ለነደፈችው ፕሮጀክቶች፣ ፕሮግራሞች  እንዲሁም ዕቅዶች  አተገባበር ጋር በመቃኘት መከለስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ ፓኬጅ ተከልሷል፡፡

በዚሁም መሠረት በዶሮ ሀብት ልማት አዋጭ የሆኑ የስራ ክፍሎች ማለትም የአንድ ቀን ጫጩት ማሳደግ/ቄብ ማምረት፣ የስጋ ዶሮ እርባታ፣ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ እና ጥምር ጠቀሜታ የዶሮ እርባታ ያላቸዉ በስራ ላይ እንዲውሉ የሚከተሉት ዝርዝር ፓኬጆች ተከልሷል፡፡ 

1.1.     የፓኬጁ አስፈላጊነት

የተሻሻለ ቴክኖልጂዎችን አሟልቶ መጠቀም የሚያስችል ድጋፍ በመስጠት የዶሮን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ

ከምርምር ማዕከለ የተገኙ ዉጤቶች እና  ከዉጪ ሀገር የሚመጡ ቴክኖሎጂዋችን ከሀገራችን  ተጨባጭ ሁኔታጋር በተገናዘበ መልኩ በማካተት የዶሮን ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል

1.2.     የፓኬጁ ዓላማ

የዶሮን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ለማሻሻል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን አሟልቶ የያዘ የኤክስቴንሽን ስርዓት ጥቅም ላይ እንዱውሉ እና ተደራሽ በማድረግ የአርሶ አደሩን እና የአርቢዉን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና፣የሥራ ዕድልን መፍጠርና ሀገራችን ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ማሳደግ፡፡

ዝርዝር ዓላማዎቹ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡

  • የአርቢውን  የገቢ ምንጭ አማራጮችን በማስፋት የህብረተሰቡን ገቢ በማሳደግ ኑሮው እንዲሻሻል ማገዝ ፤
  • ለዜጎች የሥራ ዕድልን መፍጠር
  • የዶሮ ስጋና እንቁላል ምርትን በመጨመር የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን (Food & Nutritional Security) በማረጋገጥና በድህነት ቅነሳ ፕሮግራም በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማድረግ ፤
  • ጤናማ ዜጋን ለማፍራት በሚደረገው ጥርት የህብረተሰቡን የፕሮቲን ፍላጎት በማሟላት የህብረተሰቡን የስነ ምግብ ይዘት ማሻሻል ፤
  • አርቢውንና ግብዓት አቅራቢዎችን በማስተሳሰር ራሱን በራሱ የሚያንቀሳቅስ የዶሮ እርባታ ስርዓት መዘርጋትና ከመንግስት ብቻ የሚጠበቀውን ድጋፍ መቀነስ እና
  • የዶሮ ሀብት ልማት ኤክስቴሽን ተደራሽ ማድረግ

1.3.         ፓኬጁ ግብ 

  • የዶሮ እርባታ ቴክኖሎጂ እና የኤክስቴንሽ አሰራርን  ለተጠቃሚ በማድረስ  ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣
  • አርቢዉ በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት እንዲያመርቱ ማስቻል፣
  • አርቢው የኑሮ ደረጃውንና የስርዓተ ምግብን  እንዲያሻሽል ማስቻል፣

1.4.     የፓኬጁ ይዘት

አነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የስጋ ዶሮ እርባታ ፤ አነስተኛና መካከለኛ የእንቁላል ጣይ ዝርያ ጫጩት በማሳደግ ቄብ ማምረት ፤ አነስተኛና መካከለኛ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ በማካሄድ ዕንቁላል ማምረት እና በከፊል የቤት ውስጥ (Semi-intensive) 25 ጥምር ጠቀሜታ ያላቸዉ የዕንቁላልና የሥጋ (Dual Purpose) ቄብና ኮከኔዎችን ማርባት ያካትታል፡፡

2.   የስጋ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

2.1.     አነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የስጋ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

ፓኬጁ የሚተገበረው መሰረት ልማት በተሟላባቸው አካባቢዎች በአነስተኛና መካከለኛ አርቢዎች የሚተገበር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው  የእርባታ ዘርፍ ነው፡፡ ስለሆነም አነስተኛ ደረጃ የስጋ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ ማለት ከ200 እስከ 1,500 ዶሮዎች በአንድ የእርባታ ዙር የሚይዙ ሲሆን ከ1,501 እስከ 5,000 ዶሮዎች በአንድ የእርባታ ወቅት የሚይዙት ደግሞ በመካከለኛ የስጋ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ የሚካተቱ ይሆናል፡፡ የዚህ አማራጭ ፓኬጅ ዓላማ የስጋ ዝርያ ያላቸው የአንድ ቀን ጫጩቶችን እስከ 42-56 ቀን የስጋ ዶሮ በማርባት ለእርድ ማቅረብ ነው፡፡

2.2.     ለስጋ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ ጥንቅሮች

ሀ. ዝርያ

የሥጋ ዝርያ ጫጩቶች፡- በሀገራችን በአብዛኛው አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉት ኮብ 500 (cobb 500)፤ ሮስ 308 (Rose 308) እና ሁባርድ (Hubard) የስጋ ዝርያ ዶሮዎች ሲሆኑ እነዚህንና ሌሎች አዳዲስ የስጋ ዝርያ ዶሮ ጫጩቶች ምንጭ በአሁኑ ሰዓት የስጋ ጫጩት ከሚያቀርቡ የግልና መንግስት ማባዣ ማዕከላት ይሆናል፡፡ የዶሮ ማራቢያና ማባዣ ማዕከላት ስልጣን ባለው አካል በየጊዜው  በመገምገም የማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሚሰጥበት አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ለ. መኖ

የሥጋ ዶሮዎች  በፍጥነት አድገው ለገበያ መቅረብ ስላለባቸው ጥራት ያለው የተመጣጠነ መኖ በማንኛውም ወቅት ያለገደብ ማግኘት አለባቸው፡፡መኖዎቹ በሁለት ደረጃ የተዘጋጁ ሲሆኑ እነዚህም የጀማሪዎች መኖ (Starter ration) ከተፈለፈሉ ጊዜ ጀምሮ እስከ 3 ሣምንት ዕድሜ  እና የማወፈሪያ መኖ (Finisher ration) ከ3 ሣምንት ዕድሜ እስከ ሽያጭ ጊዜ  ናቸው፡፡የስጋ ዶሮ  የተመጣጠነውን መኖ ከመኖ አምራች ድርጅቶች ወይም ጥሬ ዕቃውን ገዝቶ በተሰጡት የመኖ ቀመር አማራጮች ላይ ተመስርቶ በባለሙያ ድጋፍ ምጥን መኖ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

የመኖ ብክነትን መከላከል

በመኖ ብክነት ምክንያት የሚመጣ አላስፈላጊ ወጪን ለመቀነስ በመመገቢያዎች ውስጥ ያለውን የመኖ መጠን በመቀነስ ሲያስፈልግ እየተከታተሉ መጨመር ይገባል፡፡መመገቢያ ዕቃዎች 2/3ኛ ድረስ ከሞሉ ወደ 10% የሚጠጋ መኖ ሊባክን ይችላል፡፡ ይህን መጠን ወደ 1/3ኛ ዝቅ በማድረግ ብክነቱን ወደ 1% ማውረድ ይቻላል፡፡

ሰንጠረዥ1 የስጋ ዶሮዎች አማራጭ የመኖ ቀመሮች

የግብዓት ዓይነትየጀማሪዎች የስጋ ጫጩቶች አማራጭ ቀመሮችየሚወፍሩ የሥጋ ዶሮች አማራጭ ቀመሮች
123123
በቆሎ5053.658436254.6
የአኩሪ አተር ፋጉሎ  20  13
የለውዝ ፋጉሎ401510153019
ዘይት    1.72
ሞላሰስ 5   3
የእንስሳት ስብ4  2  
የተፈጨ አሳ 4 6 3
የተፈጨ አጥን 1.4424.64
የኖራ ድንጋ      
የተፈጨ ሥጋ  6.45  
የተፈጨ ሥጋና አጥንት4.52    
ፉሩሽኬሎ/ፊኖ 8.3 25.50.2 
L-ላይሲን0.20.40.40.30.30.2
DL-ሜታዪኒን0.10.20.20.20.20.2
ጨው0.50.50.50.50.50.5
የቫይታሚንና ንዑስ  ማዕድናት ቅይጥ0.50.50.50.50.50.5
ድምር99.890.9100100100100
የድብልቅ መኖው የሃይል ሰጪ ይዘት (ኪሎ ካሎሪ/ኪሎ ግራም መኖ)312028792930283030753013
የድብልቅ መኖው የፕሮቲን ይዘት(%)22.122.4424.321.6419.1422.05
የሃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ ፍላጎት30003200
የፕሮቲን ፍላጎት22%20%

ሐ. ጤና

ለስጋ ዶሮዎች የክትባት ፕሮግራም በእንስሳት ጤና ተቋም በሚወጣው የክትባት መርሀ ግብር መሰረት እና ከመንግስት ፈቃድ ከተሰጣቸው ክትባት አቅራቢ ድርጅቶች የሚፈጸም ሆኖ የክትባት ዓይነቶችና የጊዜ ሰሌዳዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

እድሜየክትባት ዓይነትየክትባት አሰጣጥ
  1 ቀንኢንፌክሺየስ ብሮንካይት (H120)በርጭት፤ በዓይን (አፍንጫ) በውሃ
የማሬክስ በሽታ (HVT FC – 126)በመርፌ (ታችኛው አንገት ቆዳ ስር)
5-7 ቀንየፈንግል (HB1)በዓይን (አፍንጫ) በውሃ
14 ቀንጉምቦሮ IBDበውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ ውሀ)
25ላሶታ + IBበውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ ውሀ)
40ላሶታበውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ ውሀ)
  • በሽታ መከላከል

የዶሮ በሽታ ከመከሰቱ በፊት መከላከል የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ የበሽታ ፍንዳታ ይከሰታል ተብሎ የሚጠረጠርባቸው ወቅቶች ላይ በባክቴሪያ አማካኝነት ለሚመጡ በሽታዎች አንቲ ባዮቲክ እንደ አሞክሳሲሊን፤ ኦክሲ ቴትራ ሳይክሊን፣ ኢንሮፍላክሳስሊን፣ ታይሎሲን እና ዶክሲ ቴትራ ሳይክሊን የመሳሰሉትን እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በኮክሲዲዮሲስ (coccidiosis) አማካኝነት ለሚመጣ በሽታ የፀረ ኮክሲዲዮሲስ መድኃኒት (Anti-Coccidiosis Drug) አምፕሮሊየና ሰልፎናማይድ ፕሪቬንቲቭ ዶዝ (Amprolium Preventive Dose) እንደ አሰፈላጊነቱ ቢሰጥ ጥሩ ነው፡፡ ሆኖም ለዶሮዎቹ የተሰጡት መድሀኒቶች ዶሮዎቹ ከመታረዳቸው በፊት የመድሀኒቱ ቅሪት ከዶሮዎቹ ሰውነት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚወገድበት ጊዜ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፡፡

የመከላከያ መድሀኒቶችን ስንጠቀም የመድሀኒቱን የአጠቃቀም መመሪያና የባለሙያ የምክር አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

መ. ስነ-ህይወት ጥበቃ

  1. ዶሮዎችን ለይቶ ማርባት
  2. በአንድ እርባታ ውስጥ አንድ የዶሮ ቤት ብቻ እንዲኖር ማድረግ፤ ካልተቻለ በቤቶች መካከል ቢያንስ የ12 ሜትር ርቀት ሊኖር ይገባል ሆኖም እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲሁም የበሽታ የመከሰት እድል የሚታይ ይሆናል፣
  3. እርባታው ከመኖሪያ ቤት፣ ከመንገድና ከሌሎች እርባታዎች ቢያንስ 300 ሜትር መራቅ አለበት፤
  4. በእርባታው ቤት ውስጥ አንድ ዓይነት ዕድሜና አንድ ዓይነት ዝርያ ያላቸውን ዶሮዎች ማቆየት (አንድ ጊዜ የገቡ ዶሮችን በአንድ ጊዜ ማውጣ) ተገቢ ነው፡፡
    1.  የቤት አሠራር 
  • የዶሮ ቤት ሲሰራ ረጅሙና ለአየር መዘዋወሪያ የሚተው አቅጣጫ ከጸሀይ መውጫና መግቢያ ተቃራኒ መሆን አለበት፣
  • ወፎችን ሙሉ በሙሉ የሚከላከል መሆን አለበት፡፡
  • መግቢያ በር ላይ ሰው ረግጦት የሚገባ የፀረ-ተዋስያን መድሃኒት ዲስ ኢንፌክታንት (Dis-Infectant) እንደ ባዮ ሴፍ (bio-safe)፣ቫይሮሲዳ፣ H7 እና ፎሮማሊን (formalin) ጐድጐድ ባለ ሥፍራ ላይ እንዲኖር ማድረግ እና ወቅቱን ጠብቆ መቀየር ተገቢ ነው፡፡ 
  • ወለሉ በቀላሉ ሊፀዳ በሚችል መሆን አለበት፡፡
    •  ሠራተኞች ሊያደርጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
  • አንድ ሰራተኛ ለአንድ ዶሮ ቤት መመደብ አስፈላጊ ነው፡፡
  • ከዶሮዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠራተኞች ስለ ዶሮ ጤና አጠባበቅ ጥንቃቄዎችን የሥራ ላይ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው፡፡
  • ሠራተኞች እንደ እርባታው ደረጃ የሥራ ልብስ /የራስ መሸፈኛ፤ ቱታና ቦት ጫማዎች/ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 
  • የውጪ ጎብኚዎች እርባታው ውስጥ መግባት የለባቸውም፣ መግባት ካለባው በእርባታው የተዘጋጀውን የስራ ልብስ ለብሰው መግባት አለባቸው፡፡ 
  • የእርባታው ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ቢቻል የራሳቸው የዶሮ እርባታ የሌላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  •  የንፅህና አጠባበቅና ቁጥጥር 
  • ከዶሮዎች ቤት አካባቢ ጥሻ፣ የቆሻሻ ክምችት፤ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቁሳቁስ ክምችት ለአይጦችና ሌሎች በሽታ አስተላላፊዎች መደበቂያና መራቢያ ስለሚሆን መወገድ አለበት፡፡ 
  • ጥቅም ላይ የዋለ የዶሮ ቤት ጉዝጓዝ ከዶሮዎች ቤት ሲወገድ ቢያንስ 300 ሜትር ያህል መራቅ አለበት፡፡ 
  • የሞቱ ዶሮዎች በድን መቅበሪያ ጉድጓድ ውስጥ ማቃጠል ወይም መቅበር ያስፈልጋል፡፡ 
  • አዲስ ዶሮዎች ከመግባታቸው በፊት ቤቱን እና ቁሳቁሶችን በሚገባ በማፅዳት ፀረ-በሽታ አስተላላፊ ተረጭቶ ለሁለት ሣምንታት/ለአንድ ወር/ ያህል ባዶውን መቆየት አለበት፡፡ 
  • ህክምና

ከጥንቃቄ በኋላ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች አስፈላጊውን ህክምና በባለሙያ እንዲሰጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 

. የዶሮ እርባታ መጠለያ ማዘጋጀት

ለዶሮዎቹ መጠለያ የዶሮዎችን ቁጥርና አቅምን ባገናዘበ መልክ ይሠራል፡፡ እርባታው የሚከናወነው በወለል ላይ ሆኖ ወለሉ ኮንክሪት ቢሆን ይመረጣል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በደንብ በተደለደለ አሸዋና አፈር መጠቀም ይቻላል፡፡ የቤቱን ሙቀት ለመጠበቅና የዶሮዎቹን ኩስ በቀላሉ ማስወገድ እንዲቻል ጉዝጓዝ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ለጉዝጓዝነት በአካባቢው የሚገኙ እርጥበት የሌላቸው እንደ ጭድ፣ ገለባ፣ የቡና ገለባና የእንጨት ፍቅፋቂ መጠቀም ይቻላል፡፡ የጉዝጓዙ ውፍረት እንደ አካባቢው የሙቀት መጠን ከ6-12 ሳ.ሜ ሆኖ በየጊዜው በመቧጠጫ (ሬክ) ማገላበጥና የሳሱና የረጠቡ ቦታዎችን በአዲስ መተካት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም መጠባበቂያ ጉዝጓዝ ማዘጋጀት ተገቢ ይሆናል፡፡

የሚሠራው ቤት እንደ ዶሮዎቹ ብዛት የሚወሰን ሆኖ በቂ የአየር እንቅስቃሴና ብርሃን ሊኖረው ይገባል፡፡ በመሆኑም የቤቱ አቀማመጥ ወርዱ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ይዞ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም ረጅሙና ለአየር መዘዋወሪያ የሚተው አቅጣጫ ከጸሀይ መውጫና መግቢያ ተቃራኒ መሆን አለበት፡፡ የሥጋ ዶሮ እርባታ ቤት ሲሰራ የወለል ስፋት ታሳቢ የሚደረገው በአማካይ 10 ዶሮዎች በካሬ ሜትር ማሳደግ ይቻላል፡፡ በቀዝቃዛ አካባቢ ይህ መጠን በ10% ሊጨምር ይችላል፡፡/11 ዶሮዎች በካሬ ሜትር/፡፡ በሞቃታማ አካባቢዎች ግን ይህ መጠን በ10% መቀነስ አለበት፡፡ 9 ዶሮዎች በካሬ ሜትር ሆኖ መሰራት አለበት፡፡

የዶሮ ቤት ሢሠራ የሚከተሉትን መሠረታዊ ታሳቢዎች ማሟላት ይኖርበታል፣እነዚህም 

  • ዶሮዎችን ከጥቃት የሚከላከል፡- ዶሮዎችን ከሚያጠቁ አውሬዎች የሚከላከልና ለውጪ ጥገኛ ተሃዋስያን መራባት የማያመች መሆን ይኖርበታል፡፡
  • የግድግዳ አሠራርን በተመለከተ፡- እንደ አየሩ ሁኔታ በቤቱ ረዥም ወገን ግራና ቀኝ የሚገኙ ሁለት ግድግዳዎች ከግማሽ በላይ እንደመረብ በተሠራ ሽቦ ተሸፍነው ክፍት መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም በተለይ ነፋስ የሚኖርበት ወገን እንዲሁም አካባቢው ማታ ወይንም በአንዳንድ ወቅቶች የመቀዝቀዝ ባህሪ ካለው ሊጠቀለልና ሊዘረጋ በሚችል ወፈር ያለ የላስቲክ ወይም ተመሳሳይ ለመሸፍን በሚያስችል ግርዶሽ መሰራት ይኖርበታል፡፡
  • እርጥበታማ በሆኑ አካባቢዎች ጣሪያው ብዙ የዝናብ ውሃ እንዲያወርድ ስለሚያስፈልግ የጣሪያው ተዳፋት ከፍተኛ መሆን አለበት፡፡
  • የዝናቡ ውሽፍር (ፍንጣቂ) ወደ ዶሮዎቹ ቤት እንዳይገባ የጣሪያው ክፈፍ ከግድግዳው አንድ ሜትር ያህል መርዘም አለበት፣
  • በቤቱ ውስጥ በቂ የአየር እንቅስቃሴ እንዲኖር የቤቱ ግድግዳ ከፍታ እንደ አካባቢው አየር ሁኔታ ከ2.5 እስከ 3.7 ሜትር መሆን አለበት፡፡

የዶሮ ቤት አሰራር ስዕል

ተመራጭ የዶሮ ቤት አቀማመጥ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ መሰራት አለበት

(Orientation፡ East-West direction)

  • የዶሮ ቤት መገልገያ ቁሳቁሶች

በመጠለያ ቤት ውስጥ ለዶሮዎቹ/ጫጩቶች የሚያስፈልጉ መገልገያ ቁሳቁሶች መጠጫ፣ መመገቢያ፣ ማሞቂያና ጫጩት መከለያ ሲሆኑ አነዚህም ሊሰበሩ ስለሚችሉ መጠባበቂያ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

  • የጫጩት ውሀ መጠጫ (አንድ የውሀ ማጠጫ ለ50  ጫጩት ይሆናል)
  • ለአንድ ታዳጊ ዶሮ መመገቢያ (8 ሣ.ሜ.)
  • ለታዳጊ ውሀ መጠጫ (2 ሣ.ሜ. ለ1 ዶሮ) አቅርቦት ሊኖር ይገባል፡፡
  • የጫጩት ማሞቂያ (ኢንፍራሬድ አምፑል ወይም ባለ 60 ዋት አምፑሎችን መጠቀም የሚቻል ቢሆንም 100/200/ ዋት አምፑል መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡
  • የኤሌክትሪክ ሀይል በሚቋረጥበት ጊዜ ተቀጣጥሎ ያበቃለት ከሰል፣ ፋኖስ፣ ባዮ ጋዝ በጥንቃቄ መጠቀም ይቻላል፡፡
  • ጫጩቶች በየቦታው እየሄዱ በሰራተኛው እንዳይረገጡና እንዳይደራረቡ እንዲሁም ሙቀቱን በተፈለገው ቦታ ላይ ለመወሰን ከ45-50ሴ.ሜትር ከፍታ ያለው ክብ ቅርጽ ግርዶሽ ከ500 ለማይበልጡ ጫጩቶች ማዘጋጀትና በመከለል እስከ ሁለት ሳምንት ካቆዩ በኋላ በቤት ውስጥ መልቀቅ ያስፈልጋል፡፡

ረ. አረባብና አያያዝ (husbandry and management)

የሥጋ ዝርያ ዶሮዎች እርባታ ከጫጩት ማሳደግ ጀምሮ የሚካሄድ ተግባር በመሆኑ በዚህ ሥራ የጫጩቶች አያያዝ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ በጫጩት አስተዳደግ ወቅት የሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት የሚሹ ናቸው፡፡

  • የጫጩት ማሳደጊያ ቤት ሌሎች ቄብ፣ ኮከኔና እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ካሉበት ቤት ከ15 እስከ 30 ሜትር መራቅ አለበት፡፡
  • በማሳደጊያው ውስጥ ከአንድ በላይ የጫጩት ቤቶች ቢኖሩ በቤቶቹ ውስጥ የተለያየ ዕድሜ ያላቸው ጫጩቶች መኖር የለባቸውም፡፡ የዕድሜ ልዩነቱ እንኳን ቢኖር ከ7 ቀን በላይ ሊሆን አይገባም፡፡

የብርሃን ሁኔታ

  • ጫጩቶች በተለይ ለመጀመሪያዎቹ 48 ሰዓታት ያለማቋረጥ በቂ ብርሀን ማግኘት አለባቸው፡፡ ይህ ጫጩቶቹ መብላትና ውሃ መጠጣት እንዲጀምሩ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በሚጠጡት ውሃ ላይ የሚንፀባረቀው ብርሃን እንዲጠጡ ይጋብዛቸዋል፡፡
  • ከ48 ሰዓት በኋላ የብርሃን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከዚህ በኋላ ጫጩቶች በየቀኑ የ23 ሰዓት ብርሃን ማግኘት አለባቸው፡፡ ለአንድ ሰዓት መብራት እንዲጠፋ የሚደረገው በአጋጣሚ መብራት ቢጠፋ እርስ በርሳቸው ጉዳት እንዳያደርሱና የጨለማውን ሁኔታ እንዲለማመዱት ሲባል ነው፡፡
  • ለሥጋ ዶሮች የ23 ሰዓት ብርሃን የሚሰጠው በአጭር ጊዜ ለገበያ መድረስ ስላለባቸው በተቻለ መጠን ያለማቋረጥ እንዲመገቡ ነው፡፡ 

የሙቀት ሁኔታ

  • ጫጩቶች ከመግባታቸው 12 ሰዓት በፊት ቤቱ እንዲሞቅ ማሞቂያዎቹን መለኮስ ተገቢ ነው፡፡ ለሥጋ ዝርያ ጫጩቶች ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሁለተኛው ቀናቸው የቤቱ ሙቀት 30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሙቀት መጠን ሆኖ ከሶስት እስከ ሃያ ሰባተኛው ቀን ድረስ ያለው በየቀኑ በ 1 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እየቀነሰ በሃያ ሰባተኛው ቀን 20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ማድረስ እና ከአካባቢው ሙቀት ጋር ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡
  • የጫጩቶች የማሞቂያዉ (Brooder) ሥር የሙቀት መጠን ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሁለተኛው ቀን 32 ዲግሪ ሴንቲግሬ ሆኖ ከሶስት እስከ ሃያ ሰባተኛው ቀን ድረስ ያለው እንደ አስፈላጊነቱ ከ 1 እስከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬ እየቀነሰ በሃያ ሰባተኛው ቀን 20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መድረስ ይኖርበታል፡፡ Looking Chick behaviour is the best indicator of correct temperature!
  • የመከለያው የሙቀት መጠን ከማሞቂያው ስር 2 ሜትር ርቀት በስተ ቀኝና በስተግራ በኩል ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሁለተኛው ቀን 29 ዲግሪ ሴንቲግሬ ሆኖ ከሶስት እስከ ሃያ ሰባተኛው ቀን ድረስ ያለው እንደ አስፈላጊነቱ ከ 1 እስከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬ እየቀነሰ በሃያ ሰባተኛው ቀን 20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መድረስ ይኖርበታል፡፡          
  • ማሞቂያዎች ከወለል ያላቸውን ከፍታ በመጨመር የሙቀቱን መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡  ጫጩቶች በተለይ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሣምንታት ዕድሜያቸው በቀላሉ ይረበሻሉ፡፡ ፈጣን የሙቀት፣ የብርሃን፣ የአየር እንቅስቃሴ፣ የውሃና መኖ አቅርቦት መጠንና ዓይነት ለውጦች እንዲሁም ከፍተኛ ድምፅ በቀላሉ ስለሚረብሻቸው ዕድገታቸው ይታወካል፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓይነት ለውጦችን በተቻለ መጠን ላለማድረግ መጣር ያስፈልጋል፡፡

ሠንጠረዥ1. ከጫጩቶቹ እድሜ ጋር ተፈላጊ የሙቀት መጠን

የጫጩት ዕድሜ በቀንየቤቱ የሙቀት መጠንየማሞቂያው ስር (Brooder) የሙቀት መጠንየመከለያው የሙቀት መጠን ከማሞቂያው በቀኝና በግራ 2 ሜትር ርቀት 
 የአንድ ቀን303229
3283027
6272825
9262725
12252625
15242524
18232424
21222323
24212222
27202020

የውሃ አቅርቦት 

ጫጩቶች ከመድረሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ውሃ /18 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ወይም በመጠኑ ከዚህ ከፍ ያለ/ መዘጋጀት አለበት፡፡ ብዙውን ጊዜ ጫጩቶች ምግብ ከመብላታቸው በፊት ውሃ ስለሚጠጡ በመጀመሪያው ቀን በሚሰጣቸው ውሃ ውስጥ 8% ያህል ስኳር ማሟሟት /80 ግራም በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ በጥብጦ መስጠት/ ጫጩቶቹ በቂ ኃይል እንዲያገኙ ይረዳል፡፡ ጫጩቶቹ ከረዥም ርቀት ጉዞ በኋላ ተጐድተው የሚደርሱ ከሆነ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀ ከቪታሚንና ማዕድናት ድብልቅ  በውሃ አሟሙቶ ከ3-4 ቀናት መስጠት በሽታን ለመቋቋም ያግዛል፡፡ የመጠጫ ቦታ ስፋትን በተመለከተ ለአንድ ዶሮ በረዥም ማጠጫ 2 ሣ.ሜ ሂሣብ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ በክብ ማጠጫ 20% ተጨማሪ ጫጩቶችን ማጠጣት ይቻላል፡፡

ሰ. ከአርቢው የሚጠበቁ መስፈርቶች

  • ለዶሮ እርባታ ሥራ ከፍተኛ ፍላጐት ያለው፣
  • የሚሰጠውን ምክርና የአሠራር ዘዴ ተቀብሎ ለመተግበር ፈቃደኛ የሆነ፣
  • ያገኘውን ልምድ ለሌሎች ለማካፈል ጥረት የሚያደርግ፣
  • የገቢ ምንጭ የሌላቸው ሴቶችና ሥልጠና የወሰዱ ወጣቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፣
  • ቀደም ሲል ብድር ወስዶ ከነበረ ብድሩን በወቅቱ የመመለስ ታሪክ ያለው ፤
  • በከተሞችና በገጠር አካባቢ ለሚደራጁ ወጣቶችና ሴቶች የቦታ አቅርቦት በተመለከተ በአካባቢው መስተዳድር የሚመቻች ሲሆን
  • ከተማ መስተዳድሩ ለዶሮ እርባታ የሚያዘጋጃቸው ሼዶች ለዶሮዎች አመቺ እንዲሆን ከእንስሳት እርባታ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
  • እነዚህ በክላስተር ተደራጅተው ያረቡዋቸውን ዶሮዎች ተቀብሎ በማረድ ለተለያዩ ተጠቃሚዎች የሚያቀብል የዶሮ ቄራ በአካባቢያቸው  እንዲቋቋም ይደረጋል፡፡

. ለአነስተኛ የስጋ ዶሮ እርባታ የግብዓት ፍላጐት /ጥንቅር/ (በምሳሌነት ለ1000 ዶሮዎች የቀረበ)

ተ.ቁየግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣የመኖማከማቻናካ.ሜ1105,000.00
2ማግለያካ.ሜ65,000.00
3መጠጫቁጥር20260.00
4መመገቢያቁጥር20260.00
5አካፋቁጥር2170.00
6ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120.00
7የእጅ ጋሪቁጥር13,500
8የዉሃ ማጠራቀሚያ(ባለ1000ሊ)ቁጥር14,500.00
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር2600.00
10ብሩደር ባለ 200W አምፑል የተገጠመለትቁጥር22,500.00
11መከለያ /ግርዶሽ/ሜትር6025.00
12ክትባት ማጓጓዣ አይስ ቦክስቁጥር12,500.00
13መዝገብቁጥር1130.00
14መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11000.00
15የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር23200.00
16የስጋ ዝርያ ጫጩቶችቁጥር100060.00
17መኖ (Feed)ኪ.ግ400040
18ክትባትዶዝ70000.50
19መድሃኒትና ቫይታሚን,3,500
20ጉዝጓዝኩንታል30100.00
21ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፈክታንት)ሊትር2150.00
 የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪዙር12,500

. የሥርጭት አካባቢዎች

  • ይህ ፓኬጅ የምርት ግብዓት /በተለይ መኖ/ እንዲሁም ገበያ በተመቻቸባቸው ከተሞችና ከተሞች ዙሪያ  (Urban /Peri-urban) መካሄድ ያለበት ነው፡፡
  • የሥጋ ዶሮዎች እርባታ ከሌሎች የዶሮ እርባታ ዘርፎች በተለይ ዶሮዎቹ በደረሱ ጊዜ ወደ ገበያ ወዲያው መውጣት ካልቻሉ ብዙ ችግር ሊያስከትል የሚችል ስለሆነ የገበያ ትስስር ስርአት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

    ሸ. ለስጋ ዶሮች ፓኬጅ የአዋጭነት ስሌት

  • የአዋጭነት ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖረው ግብዓት ወጪና የምርት መሸጫ ዋጋ ላይ ተመሥርቶ የሚለዋወጥ ቢሆንም በአማካይ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ እንደሚከተለው ተሰልቷል፡፡
  • አንድ የሥጋ ዶሮ አምራች በዓመት 4 ዙር ማለትም በ6 ሳምንት ዕድሜ ለገበያ በማቅረብና በሚቀጥለው ዙር ጫጩቶች ከመግባታቸው በፊት የስነ-ህይወት ደህንነት የዕረፍት ጊዜ ቢኖር በሚል የተሰላ ነው፡፡
  • አርቢው በየዙሩ 1000 ጫጩቶች እንደሚያሳድግ ታሳቢ ተደርጐ የተሠራ የአዋጪነት ስሌት፣

ሰንጠረዥ1 የቋሚ እቃ ወጪዎች

ተ.ቁየግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣የመኖማከማቻናካ.ሜ1105,000.00550,000
2ማግለያካ.ሜ65,000.0030,000
3መጠጫቁጥር20260.005,200
4መመገቢያቁጥር20260.005,200
5አካፋቁጥር2170.00340
6ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120.00120
7የእጅ ጋሪቁጥር13,5003,500
8የዉሃ ማጠራቀሚያ(ባለ1000ሊ)ቁጥር14,500.004,500
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር2600.001,200
10ብሩደር ባለ 200W አምፑል የተገጠመለትቁጥር22,500.005,000
11መከለያ /ግርዶሽ/ሜትር6025.001,500
12ክትባት ማጓጓዣ አይስ ቦክስቁጥር12500.002,500
13መዝገብቁጥር1130.00130
14መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11000.001,000
15የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር23200.006,400
ጠቅላላ ድምር616,590

ሰንጠረዥ 2 የቋሚ እቃዎች የአገልግሎት ዘመንና ተቀናናሽ ወጪ

ተ/ቁየግብዓት አይነትመለኪያጠ/ዋጋየአገልግሎት ዘመንየ1 ዓመት ተቀናናሽ ወጪየ1 ዙር ተቀናናሽ ወጪ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ፣ መኖ ማከማቻ) ማረፊያ፣የመኖማከማቻናካ.ሜ550,0001536666.679166.667
2ማግለያካ.ሜ30,000152000500
3መጠጫቁጥር5,20031733.333433.3333
4መመገቢያቁጥር5,20051040260
5አካፋቁጥር34056817
6ሬክ/መቧጠጫቁጥር12010123
7የእጅ ጋሪቁጥር3,5001035087.5
8የዉሃ ማጠራቀሚያ(ባለ1000ሊ)ቁጥር4,50010450112.5
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር1,2002600150
10ብሩደር ባለ (200W አምፑል የተገጠመለትቁጥር5,00051000250
11መከለያ /ግርዶሽ/ሜትር1,50011500375
12ክትባት ማጓጓዣ አይስ ቦክስቁጥር2,5001025062.5
13መዝገብቁጥር1305266.5
14መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር1,0001010025
15የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር6,40010640160
 ጠቅላላ ድምር 616,59046,436.00311609.0003

ሰንጠረዥ 3 የተንቀሳቃሽ እቃዎች ወጪ

ተ.ቁየግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ የ1 ዙር ወጪጠቅላላ የ1 ዓመት ወጪ
1የስጋ ዝርያ ጫጩቶችቁጥር100060.0060,000240,000
2መኖ (Feed)ኪ.ግ400040160,000640,000
3ክትባትዶዝ70000.503,50014,000
4መድሃኒትና ቫይታሚን, 3,50014,000
5ጉዝጓዝኩንታል30100.003,00012,000
6ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፈክታንት)ሊትር2150.003001,200
7የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪዙር12,5002,50010,000
 የአላቂ ዕቃዎች ወጪ ድምር   232,800931,200
የአገልግሎት ተቀናሽ   11,609.000346,436.003
 የወጪ ድምር   244,409.0003977,636.003
መጠባባቂያ (5%) 12,220.4548,881.80
.ጠቅላላ የወጪ ድምር256,629.001,026,517.00

ሰንጠረዥ 4 የገቢ ስሌት

 ተ.ቁየገቢ ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ የ1 ዙር የገቢ ስሌትጠቅላላ የ1 ዓመት የገቢ ስሌት
1የሥጋ ዶሮዎች ሽያጭቁጥር950425403,7501,615,000
2ከዶሮ ኩስ ሽያጭኩ/ል201503,00012,000
ጠቅላላ ገቢብር406,7501,627,000
ጠቅላላ ወጪብር256,629.001,026,517.00
ያልተጣራ ትርፍብር150,121600,483

ማጠቃለያ፡-

  • በግል/በቡድን የተደራጀተው ጫጩት አሳዳጊዎች በ1 ዙር (በ6 ሳምንት) ውስጥ የሚያገኙት ትርፍ ብር 150,121 ሲሆን  በዓመት (በ 4 ዙር) ብር 600,483 ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡

ታሳቢዎች፡-

  • የሞት መጠን 5% ታሳቢ ተወስዷል ስለሆነም 1000X5% = 950 የስጋ ጫጩቶች ያድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • 6 ሳምንት የሆነው የስጋ ዶሮ 2.3ኪ/ግ ክብደት የሚመዝን ሲሆን የስጋ ምርታማነት የቁም ክብደቱን 72% ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የተገኘ የስጋ ምርት ከአንድ ዶሮ 1.7 ኪ/ግ ነው፡፡
  • ለወጪው መጠባበቂያ 5% ታሳቢ ተወስዷል፡፡

3.   የአንድ ቀን ጫጩት ማሳደግ/ቄብ ማምረት ፓኬጅ

አነስተኛና መካከኛ የእንቁላል ጣይ እና ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ርያ ጫጩቶችን በማሳደግ የ45 ቀን ጫጩት እና የ3 ወር ቄብ ዶሮዎችን የማምረት ፓኬጅ

በየክልሉ ያሉ የመንግስት የዶሮ ማራቢያና ማባዣ ማዕከላት እንዲሁም በጫጩት ማስፈልፈል ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች የሚያመርቷቸውን የእንቁላል ጣይ ወይም ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው የዶሮ ዝርያ የአንድ ቀን ጫጩቶችን እንዲሁም ሌሎቸ አስፈላጊ ግብዓቶችን በማጥናቀር የሚተገበር የዶሮ እርባታ ፓኬጅ ነው፡፡ እንደ አስፈላጊነቱና እንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ፤ ከ45 እስከ 90 ቀን ወይም 3 ወር እድሜ ያላቸው ቄብ ዶሮዎችን በማሳደግ፣ ለአነስተኛና መካከለኛ የእንቁላል ጣይ እንዲሁም ለተሻሻለ የቤተሰበ ዶሮ እርባታ ንዑስ ዘርፎች የዝርያ ግብዓት አቅራቢ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡

በከተማና በከተማ አቅራቢያ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ባለበት የሚተገበር ሲሆን፣ ለግለሰቦች፣ ለተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድልና የገቢ ምንጭ በመሆን ከፍተኛ አቅም ያለው የዶሮ እርባታ ፓኬጅ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ሀይል በሌለባቸው አካባቢዎች ተለያዩ ሰው ሰራሽ የሙቀት ማመንጫ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጫጩት ማሳደግ ይቻላል፡፡

ዚህ ፓኬጅ አነስተኛ ደረጃ የእንቁላል ጣይ ወይም ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ጫጩቶችን ማሳደግ ማለት በአንድ የእርባታ ዙር የሚያዙ/የሚያድጉ ከ1000 እስከ 1500 ጫጩቶችን ሲሆን ከ1501 እስክ 3000 ጫጩቶችን የሚይዙ/የሚያሳድጉ ደግሞ በመካከለኛ የእንቁላል እና ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ፓኬጅ ናቸው፡፡ ፓኬጁን ተግባራዊ ለማድረግ፣ የሚያስፈልጉ የግብዓቶች መጠን፣ እንደምናሳድጋቸው ጫጩቶች ቁጥር የሚወሰን ሲሆን፣ ለማሳያ ይሆን ዘንድ፣ ለ1000 የአንድ ቀን እንቁላል ጣይ/ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶችን ለ60 ቀን/2 ወር ለማሳድገ ምከናወን ያለባቸው ስራዎች ማለትም የጤናና ስነ-ህይወት ጥበቃ፣ የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች፣ የመጠለያ አሰራር፣ የሚያስፈልጉ የመገልገያ ቁሳቁሶች ፣ የቦታ ፍላጐት፣ ለደርጉ የሚገባው የአያያዝና እንክብካቢ ተመሳሳይ ስልሆነ ከዚህ በታች በየንዑ-ክፍሉ ተጠቃሎ ተቀምጧል፡፡ ይሁን እንጂ  አብዛኛዎቹ ግብዓቶችና ወጪዎች ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶች መግዣና አሳድጎ መሸጫ ዋጋ ከእንቁላል ጣይ ዝርያ ስለሚለይ የአዋጭነት ስሌት ለብቻው ተቀመጧል፡፡

3.1.     የአንድ ቀን ጫጩት ለማሳደግ ማስፈጸሚያ ስልቶች

ጫጩቶች የእንቁላል ዝርያ ከሆኑ በጾታ ተለይተው ሴቶቹን ብቻ እንዲሁም ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ከሆኑ ፆታ መለየት ስለማይቻል ሁለቱም ፆታ ወደ እርባታ በማስገባት እንዲያድጉ ይደረጋል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዝርያ ቄቦችን እንደነባርዊ ሁኔታው፣ ከ45 ቀን ጀምሮ እስከ 90 ቀን/3 ወር ባለው እድሜ ለአነስተኛና መካከለኛ የእንቁላል ዶሮ እርባታ ነዑስ-ዘርፍ የሚስራጩ ይሆናል፡፡ ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው በአርባ አምስተኛው ቀን እድሜ ለስርጭት ሲደርሱ ሴቶቹን ለተሻሻለ የቤተስብ ዶሮ እርባታ በማሰራጨት ወንዶቹን፣ ለተጨማሪ ጊዜ ለእርድ እስኪደርሱ በማሳደግ ለስጋ ገበያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ የዶሮ ብዜት ማዕከላት በመጀመሪያ ቀን መውሰድ ያለባቸውን ክትባት የወሰዱ ሙሉ ጤነኛ የሆኑ ጫጩቶችን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

 ዶሮ ዝርያ ምንጭ

የእንቁላል ጣይ ዝርያ ጫጩቶች፡- በሀገራችን በአብዛኛው አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉት ቦቫንስ ብራውን (Bovans Brown)፤ ቦቫንስ ዋይት (Bovans White) ሎህማንስ ብራውን (Lohmanns Brown)፤ ሎህማንስ ዋይት (Lohmanns White) ሲሆኑ፣ ለወደፊት በምርምር ተፈትሸው ለሃገራችን የእርባታ ስርዓት ተስማሚነታቸው የተረጋገጠ የዶሮ ዝርያዎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡ የጫጩቶች ምንጭ፣ በጫጩት ማስፈልፈል ዘርፍ የተሰማሩ በየክልሉ ያሉ የመንግስትና የግል የዶሮ ማራቢያና ማባዣ ማዕከላት ይሆናል፡፡ የሚቀርቡ ጫጩቶች በክትባት ካላንደሩ መሠረት አስፈላጊውን የመጀመሪያ ቀን ክትባት ያገኙ መሆን አለባቸው፡፡

ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶች፡- በሀገራችን በአብዛኛው አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉት ሳድሶ (Saso T44)፣ ኮኮክ (Potchefstroom Koekoek) ለወደፊት በምርምር ተዳቅለው፣ ተሻሽለው ወይም ከውጭ ሃገር ገብትው ተፈትሸው ለሃገራችን የእርባታ ስርዓት ተስማሚነታቸው የተረጋገጠ የዶሮ ዝርያዎችን የሚያካተቱ ይሆናል፡፡ የጫጩቶች ምንጭ፣ በጫጩት ማስፈልፈል ዘርፍ የተሰማሩ በየክልሉ ያሉ የመንግስትና የግል የዶሮ ማራቢያና ማባዣ ማዕከላት ይሆናል፡፡

  1. የእንቁላል ጣይ ዝርያ ጫጩቶች አመጋገብ

በመጀመሪያዎቹ 8 ሣምንታት በሚገባ የተመጣጠነ የንጥረ ምግብ ይዘት ያለው የጫጩት መኖ አቅርቦት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ደረጃ የሚሰጥ መኖ ከ 18 – 20% ፕሮቲን እንዲሁም ሃይል ሰጪ 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ ግራም መኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ አርቢው ከ 8 ሳምንት ጀምሮ እስከ 12ኛው ሳምንት ባለው ጊዜ (ለስርጭት እስከሚደርስ) የቀረውን 4 ሳምንት የተመጣጠነ የታዳጊ የዶሮ መኖ መመገብ ይኖርበታል፡፡ የጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶች፣ የፕሮቲን እንዲሁም ሃይል ሰጪ ንጥረ-ምግብ እስክ አሁን በግልፅ የተቀመጠ መረጃ ስለሌለ፣ ከላይ የተገለፀውን መጠቀም ያስፈልጋል፣ ለወድፊት በጥናት የተደገፈ መረጃ ሲኖር፣ በዚያ መሰረት መመገብ ያስፈልጋል፡፡ መኖ፣ ከዶሮ መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ወይም አስፈላጊ የመኖ ጥሬዕቃዎችን በማሟላትና ተገቢውን የመኖ ቅመራ በመከተል በግል ማዘጋጀት ይችላል፡፡ የመኖ ጥንቅሩን በተመለከተ የተያያዘውን አባሪ 4 የእንቁላል ዝርያ ዶሮዎች አማራጭ የመኖ ጥንቅሮችን ይመልከቱ??

  1. የመኖ ብክነትን መከላከል

በማነኛውም ዓይነት የዶሮ እርባታ ውስጥ እስከ 70% ድረስ የሚደርሰውን ከፍተኛ ወጪ የሚይዘው የመኖ ወጪ ነው፡፡ በመሆኑም የመኖ ከብክነትን በመከላከል በአግባቡ መጠቀምና ለዶሮዎች እንዲውል ማድረግ እርባታውን ትርፋማ ከሚያደርጉት ስልቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ የመኖ ብክነት በተለያዩ መንገዶች በተለይም በሚዘጋጅበት፤ በሚጓጓዝበት፤ በሚከማችበት ፤ ለዶሮዎች በሚሰጥበት ወቅትና ዶሮዎች ሲመገቡ ሊከሰት ይችላል፡፡ አላስፈላጊ የመኖ ብክነትን ለመቀነስ በመመገቢያዎች ውስጥ የሚጭመረውን መኖ መመጠን ያስፈልጋል፡፡ መመገቢያዎች 2/3ኛ ከተሞሉ ወደ 10% የሚጠጋ መኖ ሊባክን ይችላል፡፡ ስለሆነም ይህን መጠን ወደ 1/3ኛ ዝቅ ማድረግ ብክነቱን ወደ 1% ያወርደዋል፡፡ ጫጩቶች እያደጉ ሲሄዱ በየጊዜው ከመካከላቸው አማካይ ዕድገት ባለው የጫጩት የጀርባ ከፍታ ልክ የመመገቢያውን ከፍታ መጨመር ያስፈልጋል፡፡

  1. የውሃ አቅርቦት  

ጫጩቶች ከመድረሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ፣ እስከ18 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ውሃ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ብዙውን ጊዜ ጫጩቶች ምግብ ከመብላታቸው በፊት ውሃ ስለሚጠጡ በመጀመሪያው ቀን በሚሰጣቸው ውሃ ውስጥ 8% ያህል ስኳር በማሟሟት /80 ግራም በሊትር ውሃ ውስጥ/ጫጩቶቹ በቂ ኃይል እንዲያገኙ ይረዳል፡፡ ጫጩቶቹ ከረዥም ርቀት ጉዞ በኋላ ተጐድተው የሚደርሱ ከሆነ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀ የቪታሚንና ማዕድናት ድብልቅ በውሃ አሟሙቶ ከ3 – 4 ቀናት መስጠት በሽታን ለመቋቋም ያግዛል፡፡ የመጠጫ ቦታ ስፋትን በተመለከተ ለአንድ ዶሮ በረዥም ማጠጫ (Long Waterer) 2 ሣ.ሜ ሂሣብ እና በክብ ማጠጫ (Round Waterer) 1 ሳ.ሜ ሂሳብ እስከ 18 ሳምንት ዕድሜ ድረስ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ የጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶች፣ መጠናቸው ከእንቁላል ዝርያ ከፍ ስለሚል፣ የመጠጫ ቦታ ስፋትም አብሮ ስለሚጭምር፣ ጥበት እንዳይፈጠር በመመልከት መጨመር ያስፈልጋል፡፡

  1. የእንቁላል ጣይና ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶች ጤናና ስነ-ህይወት ጥበቃክትባት (Vaccination)          

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ውስጥ አሉ የሚባሉ የዶሮ በሽታዎችን እንደ ፈንግል (Newcastel Disease/NCD)፤ ማሬክስ (Mareks)፤ ጉምቦሮ (Infectious Bursal Diseases/IBD)፤ ኢንፌክሸስ ብሮንካይትስ (Infectious Bronchitis/IB)፣ ፈዎል ታይፎይድ (Fowl Typhoid) እና ፋዎል ፖክስ (Fowl Pox) ለመከላከል፣ የእንስሳት ሀኪሞችን በማማከርና ሙያዊ እገዛ ክትባት መስጠት ያስፈልጋል፡፡  

የዶሮዎች የክትባት ፕሮግራም በእንስሳት ጤና በሚወጣው የክትባት መርሀ-ግብር መሰረት እና ከሚመልከተው የመንግስት ዓካል ፈቃድ ከተሰጣቸው ክትባት አቅራቢ ድርጅቶች እንደአስፈላጊነቱ የሚፈፀም ሆኖ በተለይ በሚከተሉት የክትባት ዓይነቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አባሪ 2 በክትባት አሰጣጥ ወቅት ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን ይመልከቱ??

ሰንጠርዠ … ለጫጩቶች የሚስጡ ክትባቶችንና የአሰጣጥ ዘዴዎች

የጫጩት/ዶሮ እድሜየክትባት ዓይነትየክትባት አሰጣጥ ዘዴ
1ኛ ቀን ማሬክስበመርፌ (ታችኛው አንገት ቆዳ ስር)
ፈንግል/NCD በርጭት /በመርፌ /በአይን ጠብታ
ኢንፌክሸስ ብሮንካይትስ/IBበርጭት/በመርፌ /በአይን ጠብታ
10ኛ ቀንፈንግል/NCD + ኢንፌክሸስ ብሮንካይትስ/IBበርጭት፤ በዓይን (አፍንጫ) በውሃ
14ኛ ቀንጉምቦሮ/IBDበውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ ውሀ)
21ኛ ቀንፈንግል/NCD-Lasota)በውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ/የባትሪ ውሀ)
ከ25 – 28ኛ ቀንጉምቦሮ/IBDበውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ ውሀ)
42ኛ ቀንታይፎይድ (Fowl Typhoid)በመርፌ (intramuscular)
ፖክስ (Fowl Pox)በክንፍ ስር
50 ኛ ቀንፈንግል/NCD-Lasota)በውሀ ተበጥብጦ (በጉድጓድ/የተጣራ/የባትሪ ውሀ)

ክትባት አሰጣጥ ወቅት ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

  • የክትባት መድኃኒቱ በንጹህ እና ከክሎሪን ነጻ በሆነ የዝናብ፤ የጉድጓድ ወይም የምንጭ፣ የተጣራ (Sterile distilled water) ውሃ በሚፈለገው መጠን መበጥበጥ አለበት፣
  • ዶሮዎች/ጫጩቶች የክትባት መድኃኒቱን እንዲጠጡ ቀደም ብሎ ውሃ እንዲጠማቸው ማድረግ ያስፈልጋል፤
  • ክትባት ጠዋት ከ2-4 ሰአት እንዲሁም ከሰአት በኋላ ከ10-12 ሰአት ቢሰጥ ይመከራል፡፡
  • የሚበጠበጠውን የክትባት ጫጩቶች/ዶሮዎች እንደ አየር ሁኔታው በሁለት ሰዓት ውስጥ ጠጥተው እንደሚጨርሱት በመገመት መበጥበጥ ይኖርበታል፣
  • የክትባት መድኃኒቱ ከመሰጠቱ በፊትና ከተሰጠ በኋላ መጠጫው በሚገባ መጽዳት አለበት፤
  • የተበጠበጠውን የክትባት መድሀኒት ሳይጨርሱ ሌላ ውሃ አለመጨመር፤
  • በዓይን (በአፍንጫ) የሚሰጡ ክትባቶች በመድሀኒት አምራቹ ድርጅት መመሪያ መሰረት መፈጸም ይኖርበታ፣
  • ክትባት ሲሰጣቸው ዶሮዎቹ/ጫጩቶቹ ጤነኛ መሆን አለባቸው፡፡ የታመሙ ዶሮዎች መከተብ የለባቸውም
  • የክትባት ከወሰዱ በኃላ ለ3 ተከታታይ ቀናት ቫይታሚን መሰጠት አለበት፤
  • በመጨረሻም የክትባት መድኃኒቱን ብልቃጥ በአግባቡ ማስወገድ ወይም መቅበር ያስፈልጋል፡፡
    • የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች

ዶሮዎችን በሽታ ከያዛቸው በኋላ ከማከም ይልቅ በሽታው ከመከሰቱ በፊት መከላከል የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ የበሽታ ፍንዳታ ይከሰታል ተብሎ የሚጠረጠርባቸው ወቅቶች ላይ በባክቴሪያ አማካኝነት ለሚመጡ በሽታዎች አንቲ ባዮቲክ እንደ አሞክሳሲሊን፤ ኦክሲ ቴትራ ሳይክሊን፣ ኢንሮፍላክሳስሊን፣ ታይሎሲን እና ዶክሲ ቴትራ ሳይክሊን የመሳሰሉትን እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በኮክሲዲዮሲስ (coccidiosis) አማካኝነት ለሚመጣ በሽታ የፀረ ኮክሲዲዮሲስ መድኃኒት (Anti-Coccidiosis Drug) አምፕሮሊየና ሰልፎናማይድ ፕሪቬንቲቭ ዶዝ (Amprolium Preventive Dose) እንደ አሰፈላጊነቱ ቢሰጥ ጥሩ ነው፡፡ ሆኖም ለዶሮዎች የተሰጡ መድሀኒቶች ዶሮዎች ከመታረዳቸው በፊት የመድሀኒቱ ቅሪት ከዶሮዎቹ ሰውነት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚወገድበት ጊዜ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የመከላከያ መድሀኒቶችን ስንጠቀም የመድሀኒቱን የአጠቃቀም መመሪያና የባለሙያ የምክር አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

ሀ) ዶሮዎችን ለይቶ ማርባት

  • በአንድ እርባታ ውስጥ ቢቻል አንድ የዶሮ ቤት ብቻ እንዲኖር ማድረግ፤ ካልተቻለ በቤቶች መካከል ቢያንስ የ12 ሜትር ርቀት ሊኖር ይገባል፡፡ ሆኖም እንደየ አካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲሁም የበሽታ የመከሰት እድል የሚታይ ይሆናል፣
  • እርባታው ከመኖሪያ ቤት፣ ከመንገድና ከሌሎች እርባታዎች ቢያንስ 300 ሜትር መራቅ አለበት፤
  • በእርባታው ቤት ውስጥ አንድ ዓይነት ዕድሜና አንድ ዓይነት ዝርያ ያላቸውን ዶሮዎች ማቆየት (አንድ ጊዜ የገቡ ዶሮችን በአንድ ጊዜ ማውጣ) ተገቢ ነው፡፡

ለ) በሽታን ለመከላከል የሚያግዝ የቤት አሠራር 

  • የዶሮ ቤት ሲሰራ ረጅሙና ለአየር መዘዋወሪያ የሚተው አቅጣጫ ከጸሀይ መውጫና መግቢያ ተቃራኒ መሆን አለበት፣
  • ወፎችን ሙሉ በሙሉ የሚከላከል መሆን አለበት፡፡
  • መግቢያ በር ላይ ሰው ረግጦት የሚገባ የፀረ-ተዋስያን መድሃኒት ዲስ ኢንፌክታንት (Dis-Infectant) እንደነ ባዮ ሴፍ (bio-safe)፣ ቫይሮሲዳ፣ H7 እና ፎሮማሊን (formalin) ጐድጐድ ባለ ሥፍራ ላይ እንዲኖር ማድረግ እና ወቅቱን ጠብቆ መቀየር ተገቢ ነው፡፡ 
  • በተለይ ወለሉ በቀላሉ ሊፀዳ በሚችል መልክ ቢሠራ የቤቱን ንፅህና በተሻለ መንገድ መጠበቅ ያስችላል፡፡

ሐ) ሠራተኞች ሊያደርጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

  • አንድ ሰራተኛ ለአንድ ዶሮ ቤት መመደብ አስፈላጊ ነው፡፡
  • ከዶሮዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠራተኞች ስለ ዶሮ ጤና አጠባበቅ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ የሥራ ላይ ሥልጠና መስጠት አለበት፣
  • ሠራተኞች እንደ እርባታው ደረጃ የሥራ ልብስ /የራስ፣ የአፍእና የአፍንጫ መሸፈኛ፤ ቱታና ቦት ጫማዎች/ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 
  • የውጪ ጎብኚዎች እርባታው ውስጥ መግባት የለባቸውም፡፡ መግባት ካለባው ለብሰው የመጡትን ልብስ ቀይረው በእርባታው የተዘጋጀውን የስራ ልብስ ለብሰውና ሌሎች ጥንቃቄውችን አድርገው መግባት አለባቸው፡፡ 
  • የእርባታው ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ቢቻል የራሳቸው የዶሮ እርባታ የሌላቸው መሆን አለባቸው፡፡

መ) የንፅህና አጠባበቅና ቁጥጥር 

  • ከዶሮዎች ቤት አካባቢ ጥሻ፣ የቆሻሻ ክምችት፤ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቁሳቁስ ክምችት ለአይጦችና ሌሎች በሽታ አስተላላፊዎች መደበቂያና መራቢያ ሊሆን ስለሚችል መወገድ አለበት፡፡ 
  • ቀደም ሲል ጥቅም ላይ የዋለ የዶሮ ቤት ጉዝጓዝ ከዶሮዎች ቤት ሲወገድ ቢያንስ 300 ሜትር ያህል መራቅ አለበት፡፡ 
  • የሞቱ ወይም ታመው የመዳን ተስፋ የሌላቸው ዶሮዎች ለሌሎች የችግር ምንጭ ስለሚሆኑ ከዶሮዎች ቤት ርቆ ለዶሮች በድን መቅበሪያ የተቆፈረ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መጣል፣ ማቃጠል ወይም መቅበር ያስፈልጋል፡፡ 
  • አዲስ ዶሮዎች ከመግባታቸው በፊት ቤቱ /ከቁሳቁስ ጭምር/ በሚገባ ፀድቶና ፀረ-በሽታ አስተላላፊ ተረጭቶ ለሁለት ሣምንታት ያህል ባዶውን መቆየት አለበት፡፡ 

ክምና

  • ከዚህ ሁሉ ጥንቃቄ በኋላ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች አስፈላጊውን ህክምና በቴና በባለሙያ እንዲሰጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
  1. የዶሮዎች/ጫጩቶች መጠለያ አሰራር

ለጫጩቶች/ዶሮዎች መጠለያ በአካባቢ በሚገኝ ቁሳቁስ የዶሮዎችን ቁጥርና አቅምን ባገናዘበ መልክ ይሠራል፡፡ ጫጩቶቹን ለማሳደግ የወለል ዶሮ እርባታ ተመራጭ ነው፡፡ እርባታው የሚከናወነው በወለል ላይ በመሆኑ ወለሉ ኮንክሪት ቢሆን ካልተቻለም በደንብ በተደለደለ አሸዋና አፈር መጠቀም ይቻላል፡፡ የቤቱን ሙቀት ለመጠበቅና የዶሮዎቹን ኩስ በቀላሉ ማስወገድ እንዲቻል ጉዝጓዝ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ለጉዝጓዝነት የሚያገለግል በአካባቢው የሚገኙ እንደ ጭድ፣ የቡና ገለባና የእንጨት ፍቅፋቂ (እርጥበት የሌለው) መጠቀም ይቻላል፡፡ የጉዝጓዙ ውፍረት ከ 5 – 8 ሴ.ሜ እንደ አካባቢው የሙቀት መጠን ሆኖ በየጊዜው በመቧጠጫ (ሬክ) መገላበጥና የሳሱና የረጠቡ ቦታዎችን በአዲስ መተካት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም መጠባበቂያ ጉዝጓዝ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

የሚሠራው ቤት እንደ ጫጩቶቹ/ዶሮዎች ብዛት የሚወሰን ሆኖ በቂ የአየር እንቅስቃሴና ብርሃን ሊኖረው ይገባል፡፡ በመሆኑም የቤቱ አቀማመጥ ወርዱ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ይዞ መሰራት ይኖርበታል፡፡ አባሪ 3 የዶሮ ቤት አሰራር ስዕል ይመልከቱ??

የዶሮዎች ቤት እንደ አካባቢው የአየር ሁኔታው፤ የዶሮዎች የመያዝ አቅምና ካፒታል በተለያየ ደረጃና ዓይነት ሊሠራ ቢችልም የሚከተሉትን መሠረታዊ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡ 

  • ምቾት፡ምቾት ያላቸው ጫጩቶች አድገው ጥሩ ምርት ይሰጣሉ፡፡
  • አመቺነት፡ቤቱ በአመቺ ቦታ ተሰርቶ በቤቱ ውስጥ ያሉት የተለያዩ መገልገያዎች ለሥራና ለእንቅስቃሴ በሚያመች ሁኔታ መቀመጥ አለባቸው፡፡
  • ዶሮዎችን ከጥቃት የሚከላከል፡ዶሮዎችን ከሚያጠቁ አውሬዎች የሚከላከልና ለውጪ ጥገኛ ተሃዋስያን መራባት የማያመች መሆን ይኖርበታል፡፡
  • የግድግዳ አሠራርን በተመለከተ ፡- በኛ ሀገር የአየር ሁኔታ በቤቱ ረዥም ወገን ግራና ቀኝ የሚገኙ ሁለት ግድግዳዎች ከግማሽ በላይ እንደመረብ በተሠራ ሽቦ ተሸፍነው ክፍት ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ በተጨማሪም በተለይ ነፋስ የሚኖርበት ወገን እንዲሁም አካባቢው ማታ ወይንም በአንዳንድ ወቅቶች የመቀዝቀዝ ባህሪ ካለው እንደአስፈላጊነቱ ሊጠቀለልና ሊዘረጋ በሚችል ወፈር ያለ የላስቲክ ወይም ተመሳሳይ መሸፈኛ ሽቦውን ለመሸፍን በሚያስችል መልኩ መሰራት ይኖርበታል፡፡
  • እርጥበታማ በሆኑ አካባቢዎች ጣሪያው ብዙ የዝናብ ውሃ እንዲያወርድ ስለሚያስፈልግ የጣሪያው ተዳፋት ከፍተኛ መሆን አለበት፡፡ የዝናብ ፍንጣቂ ወደ ዶሮዎቹ ቤት መግባት እንዳይችልም የጣሪያው ክፈፍ ከግድግዳው አንድ ሜትር ያህል ቢረዝም ጥሩ ነው፡፡
  • በቤቱ ውስጥ በቂ የአየር እንቅስቃሴ እንዲኖር ቤቱ የተቻለውን ያህል ከፍታ ቢኖረው ይመረጣል፡፡ ትልቅ የዶሮ ቤት ከሆነ ከመሬት እስከ ድምድማቱ ያለው ከፍታ 3.7 ሜትር ያህል ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
    • የሚያስፈልጉመገልገያ ቁሳቁሶች

በጫጩቶች ማሳደጊያ ቤት ውሰጥ የሚያስፈልጉ የመገልገያ ቁሳቁሶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ እነዚህ መገልገያ ቁሳቁሶች ሊሰበሩ ስለሚችሉ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መጠባበቂያ የሚሆኑ መገልገያ ቁሳቁሶች ጭምር ማዘጋጀት ይመከራል፡፡

  • ለጫጩት መመገቢያ የሚሆን ዝርግ ትሬ ፤
  • የጫጩት ውሀ መጠጫ ፤
  • ለታዳጊ ውሀ መጠጫ ፤
  • ለታዳጊ መመገቢያ ፣
  • የጫጩት ማሞቂያወ (ኢንፍራሬድ አምፑል (ባለ 200 ሻማ/ዋት) ወይም 100 ሻማ/ዋት አምፖል የተገተመለት ከአካባቢ ቁሳቁሰ ማለትም ከብረት ወይም ከቆሮቆሮ በተዘጋጀ ብሩደር መጠቀም ይቻላል፡፡ ከ1-2 ዋት ለአንድ ጫጩት ታሳቢ ተደርጎ የሚሰላ ቢሆንም እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የኤሌክትሪክ ሀይል በሚቋረጥበት ጊዜ ተቀጣጥሎ የበቃለት ከሰል ፣ ፋኖስ ፣ ባዮ ጋዝ በጥንቃቄ መጠቀም ይቻላል፡፡
  • ጩቶች በየቦታው እየሄዱ በሰራተኛው እንዳይረገጡና እንዳይደራረቡ እንዲሁም ሙቀቱን በተፈለገው ቦታ ላይ ለመወሰን ከ 45-50 ሳ.ሜ ከፍታ ያለው መከለያ (brooder gard) በመጠቀም ክብ ቅርጽ ግርዶሽ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ የክብ ቅርጹ የቦታ ስፋት ስሌት A = πr2 መሰረት ታሳቢ ተደርጎ ከ 1 ቀን እሰከ 1 ሳምንት እድሜ ጫጩቶች በ1 ሜትር2 ለ 50 እና ከ 1 ሳምንት እስከ 2 ሳምንታት በ1 ሜትር2 ለ 25 ጫጩቶች ታሳቢ ተደርጎ ማዘጋጀት የሚቻል ሲሆን በአንድ መከለያ ውስጥ ቢበዛ ከ500 ለማይበልጡ ጫጩቶች መዘጋጀት/መከለል ይኖርብናል፡፡ በመከለያው ለሁለት ሳምንታት ካቆዩ በኋላ በቤት ውስጥ መልቀቅ ያስፈልጋል፡፡
    • የወለል ፋት /ቦታ/ ፍላጐት

አስፈላጊው የቦታ ስፋት፡ ጫጩቶችን ለማሳደግ የወለል ዶሮ እርባታ ተመራጭ ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ለጫጩቶች የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ ማለትም ማሞቂያ፣ ግርዶሽ ፣ መመገቢያ፣ ውሃ መጠጫ፣ ጉዝጓዝ ወዘተ፣ የሚይዙትን ቦታ ጨምሮ በአማካይ በሞቃታማ አካባቢ 10 ጫጩቶችን በ1 ካሬ ሜትር እና በቀዝቃዛ አካባቢ 12 ጫጩቶችን በ1 ካሬ ሜትር ታሳቢ በማድረግ የቤቱ ስፋት የሚወሰን ይሆናል፡፡  

  1. አረባብና አያያዝ (husbandry and management)

የዶሮዎች እርባታ ከጫጩት ማሳደግ ጀምሮ የሚካሄድ ተግባር በመሆኑ በዚህ ሥራ የጫጩቶች አያያዝ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ በጫጩት አስተዳደግ ወቅት የሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት የሚሹ ናቸው፡፡

  • ጫጩቶች ከማሽን እንደወጡ በመጀመሪያው ሳምንት የተነጠፈው የእንጨት ፍቅፋቂ ወደ አፋቸውና አይናቸው እንዳይገባ በጉዝጓዙ ላይ ጋዜጣ ማንጠፍ የሚመገቡትን ምግብ በዝርግ ትሪ ላይ መስጠት ከዝርግ ትሪ መመገቢያው በተጨማሪ በተነጠፈው ጋዜጣ ወይም ላስቲክ ላይ ለመጀመሪዎቹ አምስት ቀናት በአንድ ጫጩት ከ 50-70 ግራም መኖ እንዲበሉ ማድረግ ያስፈልጋል:: ይህ ተግባር ለእድገታቸው ወሳኝ ነው፡፡
  • ጫጩቶች በቀን ሊያገኙ የሚገባቸው የመኖ መጠን በዝርያው የአረባብ መመሪያ/ማንዋል መሰረት ተሰልቶ መቅረብ ይናርበታል፡፡
  • በማንኛውም ጊዜ በቂ መኖና ውሃ መኖሩን ማረጋገጥ ፤
  • ጠዋት የተሰጣቸው ውሀ ሊሞቅና ሊቆሽሽ ስለሚችል ከሰዓት በኋላ በታጠበ እቃ አዲስና ንጹህ ውሀ መቀየር ያስፈልጋል፡፡
  • ጫጩቶች እስከሁለት ሳምንት እድሜያቸው ድረስ በግርዶሽ ተከልለው መቆየት ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጫጩት ማሳደጊያ ቤት ሌሎች ከፍ ካሉ ዶሮዎች ካሉበት ቤት መራቅ አለበት፡፡
  • በማሳደጊያው ውስጥ ከአንድ በላይ የጫጩት ቤቶች ቢኖሩ በቤቶቹ ውስጥ የተለያየ ዕድሜ ያላቸው ጫጩቶች መኖር የለባቸውም፡፡ የዕድሜ ልዩነቱ ከ 7 ቀን በላይ ሊሆን አይገባም፡፡
  • አዲስ ጫጩቶችን ከመቀበል በፊት የቤቱን ዕቃዎችንና አካባቢውን በሚገባ ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡
  • በአንድ ጊዜ ወደ እርባታው የሚገቡ ጫጩቶች ቁጥር ተመችቷቸው እንዲያድጉ ከሚፈለገው በላይ መሆን የለበትም፡፡ መጨናነቅ የሞት መጠንን ከመጨመሩም በላይ በዕድገት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
  • ለታመሙ ጫጩቶች/ዶሮዎች ማቆያ አነስተኛ ቤት ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
  • በአጠቃላይ ጫጩቶች ይደርሳሉ ተብለው ከሚጠበቁበት ጥቂት ቀናት በፊት ቤቱ ውስጥ የሚያስፈልገው የመጨረሻው ዝግጀት መደረግ አለበት፡፡ ዕቃዎች ተገቢ ቦታቸውን መያዛቸውንና መብራቶች ፤ ማሞቂያዎች ወዘተ… በትክክል መስራታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
    • የብርሃን ሁኔታ መከታተል
  • ጫጩቶች በተለይ ለመጀመሪያዎቹ 48 ሰዓታት ያለማቋረጥ በቂ የመብራት ብርሃን ማግኘት አለባቸው፡፡
  • ይህ ጫጩቶቹ መብላትና ውሃ መጠጣት እንዲጀምሩ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በሚጠጡት ውሃ ላይ የሚንፀባረቀው ብርሃን እንዲጠጡ ይጋብዛቸዋል፡፡
  • ከ48 ሰዓት በኋላ የብርሃን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከዚህ በኋላ ጫጩቶች በየቀኑ የ23 ሰዓት ብርሃን ማግኘት አለባቸው፡፡ ለአንድ ሰዓት መብራት እንዲጠፋ የሚደረገው በአጋጣሚ መብራት ቢጠፋ እርስ በርሳቸው ጉዳት እንዳያደርሱና የጨለማውን ሁኔታ እንዲለማመዱት ሲባል ነው፡፡ 
  • ጫጩቶች ለ 48 ሰዓታት ያለማቋረጥ በቂ ብርሃን ካገኙ በኋላ የብርሃን መጠን ቀስ በቀስ መቀነስ ይኖርበታል፡፡ በየሳምንቱ በእኩል መጠን እየተቀነሰ ጫጩቶች 20 ሳምንታት ዕድሜ በሚሆናቸው ጊዜ ከቀን ብርሃን ርዝመት (12 ሰዓት) ጋር እንዲስተካከል መደረግ አለበት፡፡
    • ቀት ሁኔታመከታተል
  • ጫጩቶች ከመግባታቸው 12 ሰዓት በፊት ቤቱ እንዲሞቅ ማሞቂያዎቹን መለኮስ ተገቢ ነው፡፡
  • የጫጩቶች የማሞቂያዉ (Brooder) ሥር የሙቀት መጠን ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሁለተኛው ቀን 32 ዲግሪ ሴንቲግሬ ሆኖ ከሶስት እስከ ሃያ ሰባተኛው ቀን ድረስ ያለው እንደ አስፈላጊነቱ ከ1 እስከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬ እየቀነሰ በሃያ ሰባተኛው ቀን 20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ማሞቂያው የሚሰጠው የሙቀት መጠን ለጫጩቶች በቂ መሆንና አለመሆኑን ለመረዳት፣ የጫቹቶችን ሁኔታ በመመልከት መረዳት ይቻላል፡፡ Looking Chick behaviour is the best indicator of correct temperature!
  • የመከለያው የሙቀት መጠን ከማሞቂያው ስር 2 ሜትር ርቀት በስተ ቀኝና በስተግራ በኩል ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሁለተኛው ቀን 29 ዲግሪ ሴንቲግሬ ሆኖ ከሶስት እስከ ሃያ ሰባተኛው ቀን ድረስ ያለው እንደ አስፈላጊነቱ ከ1 እስከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬ እየቀነሰ በሃያ ሰባተኛው ቀን 20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መድረስ ይኖርበታል፡፡          
  • ማሞቂያዎች ከወለል ያላቸውን ከፍታ በመጨመር የሙቀቱን መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡ ጫጩቶች በተለይ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሣምንት ዕድሜያቸው በቀላሉ ይረበሻሉ፡፡ ፈጣን የሙቀት፣ የብርሃን፣ የአየር እንቅስቃሴ፣ የውሃና መኖ አቅርቦት መጠንና ዓይነት ለውጦች እንዲሁም ከፍተኛ ድምፅ በቀላሉ ስለሚረበሻቸው ዕድገታቸው ይታወካል፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓይነት ለውጦችን በተቻለ መጠን ላለማድረግ መጣር ያስፈልጋል፡፡

ሰንጠረዥ…. የጫጩቶች የሙቀት ፈላጎት በእድሜ ድረጃ

የጫጩት ዕድሜ በቀንየቤቱ የሙቀት መጠንየማሞቂያው ስር (Brooder) የሙቀት መጠንየመከለያው የሙቀት መጠን ከማሞቂያው በቀኝና በግራ 2 ሜትር ርቀት 
 የአንድ ቀን303229
3283027
6272825
9262725
12252625
15242524
18232424
21222323
24212222
27202020
  1. የፓኬጁ ስርጭትና ስልትየሥርጭት አካባቢ

ይህ ፓኬጅ የምርት ግብዓት /በተለይ መኖ/፤ የኤሌትሪክ አገልግሎት ባለበትና ገበያ በተመቻቸባቸው ከተሞችና ለከተማ ቅርብ የሆኑ (Urban/Peri-urban) አካባቢዎች መካሄድ ያለበት ነው፡፡ እነዚህም ቄቦች በአነስተኛና በመካከለኛ ደረጃ በእንቁላል ዶሮ እርባታ ለተሰማሩ ሴቶች፣ ወጣቶችና በግልና በቡድን ለተደራጁ እንዲሁም በተሻሻለ የቤተሰብ የዶሮ እርባታ ለተሰማሩ/ለሚሰማሩ አርሶ/አርብቶ አደሮች የሚሰራጩ ሲሆን በተጓዳኝ የገበያ ትስስር መደረግ ይኖርበታል፡፡

  1. ስልጠና

ጫጩቶች ጫናን (stress) መቋቋም ስለማይችሉ በዚህ ፓኪጅ የሚሰማሩ አርቢዎች ስለጫጩት አስተዳደግ ቢቂ ዕውቀትና እንዲኖራቸውና ውጤታማ መሆን እንዲችሉ፣ ተግባር ተኮር ልጥና በጫጩት አመጋገብና መኖ አያያዘ፣ ክትባት አሰጣጥና ክትባት አያያዝ፣ የጫጩት ቤት የሙቀትና የብርሃን ሁኔታን መከታተል፣ በሽታ መከላከያ ዘዴዎች፣ ሠራተኞች ሊያደርጓቸው ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች፣ የመግልገያ ቁሳቁሶች (መመግቢያ፣ መጠጫ፣ ወዘተ) የንፅህና አጠባበቅና ቁጥጥር፣ መዘገብ አያያዝ (የእርባታ ዕለት ከዕልት ሁኔታ እና ገቢና ወጪ) መስጠት ተገቢ ነው፡፡ 

  1. ብድር

በዚህ ንኡስ የዶሮ እረባታ ዘርፍ የሚሰማሩ ግለሰብ ደረጃ፣ በማህበር የተደራጁ/የሚደራጁ ወጣቶችና ሴቶች፣ ለእርባታው የሚያስፈልገውን ሙሉ ወጪ እራሳቸው እንዲሸፍኑ ይጠበቃል፡፡ አቅማቸው የማይችል እንደ ሁኔታው የፋይናስና የብድር አቅርቦትን በተመለከተ በአካባቢው ባሉ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የሚመቻች ይሆናል፡፡ ይህም በአነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ በከተሞችና በገጠር አካባቢ ለሚደራጁ ሴቶችና ወጣቶች የቦታ አቅርቦት በተመለከተ በአካባቢው መስተዳድር የሚመቻች ሲሆን ከተማ መስተዳድሩ ለዶሮ እርባታ የሚያዘጋጃቸው ሼዶች ለዶሮዎች አመቺ እንዲሆን ከእንስሳት እርባታ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. የግብዓት ፍላጐት /ጥንቅር/

ሰንጠረዥ .. የግብዓት ፍላጎት በምሳሌነት ለማሳየት፣ ለ1000 የአንድ ቀን እንቁላል ዝርያ ጫጩቶችን እስከ 60 ቀን/2 ወር በማሳደግ ቄብ ለማምረት የቀረበ፡፡

ተ.ቁየግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣ የማከማቻ/store)ካ.ሜ905,000.00
2ማግለያካ.ሜ65,000.00
3መጠጫቁጥር20230.00
4መመገቢያቁጥር20290.00
5መከለያ/ግርዶሽሜትር6050.00
6ባለ144 ሻማ/W ኢንፍራ-ሬድ አምፑ ብሩደርቁጥር21,500.00
7አካፋቁጥር2480.00
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር1190.00
9የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊ.)ቁጥር116,000.00
10የእርባታ አልባሳት (ቦት ጫማ)ቁጥር2360.00
11የእርባታ አልባሳት (ቱታ)ቁጥር2780.00
12መንቁር መቁረጫ (ዲቢከር)ቁጥር18500.00
13መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11,600.00
14የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር43,200.00
15ተንጠልጣይ ሚዛን (በኤሌክትሪክ የሚሰራ) ቁጥር14,000.00
16የክትባት ማጓጓዣ (Ice Box with Ice Bag: 10lit.)ቁጥር12,800.00
17የጫጩት መከተቢያ (Eye Dropper)ቁጥር1900.00
18መከተቢያ (የክንፍ መብጫ-Double Needle Applicator)ቁጥር1800.00
19ማስክ/ጎግል (የአይን መከላከያ)ቁጥር1150.00
20ማስክ/ጎግል (የአፈና የአፍንጫ)ቁጥር13200
21ጋሪ /Wheel-Barrow/ (ቱርክ ሰራሽ)ቁጥር16,000.00
22የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜል (የፕላስቲክ፣ ባ120 ሊትር)ቁጥር11,400.00
23ጫጩቶችቁጥር100065.00
24መኖ (Feed)ኪ.ግ200037.00
25ክትባትዶዝ11,0000.70
26መድሃኒትና ቫይታሚንበግምት5.50
27የወለል ጉዝጓዝቤል9150.00
28ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፈክታንት)በግምት3000.00
29የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪለአንድ ዙር/በግምት –4000.00

3.2.     ለቄብ ማምረት ፓኬጅ የአዋጭነት ስሌት

 

የአዋጭነት በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖረው ግብዓት ወጪና የምርት መሸጫ ዋጋ ላይ ተመሥርቶ የሚለዋወጥ ቢሆንም በአማካይ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ እስከ 60 ቀን/2 ወር ለእንቁላል ዝርያ እና ጠምር ጠቃሜታ ያላቸው ጫጩቶች/ቄቦች በቅደም ተከተል እንደሚከተለው ተሰልቷል፡፡ አንድ አሳዳጊ ወይም ማህበር የአንድ ቀን የእንቁላል ጣይ ዝርያ ወይም ጠምር ጠቃሜታ ያላቸው ጫጩቶችን በማሳደግ፤ የ60 ቀን ዕድሜ ያላቸው ጫጩቶችን/ቄብ ዶሮዎችን በዓመት አራት ዙር አሳድጎ ለገበያ በማቅረብና በሚቀጥለው ዙር ጫጩቶች ከመግባታቸው በፊት የአሰራምስት ቀን ዕረፍት ጊዜ ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ ነው፡፡ በየዙሩ 1000 ጫጩቶችን ታሳቢ ተደርጐ የተሠራ ቢሆንም እንደ ሁኔታው ተጨማሪ ጫጩቶች ማሳደግ ይችላል፡፡ ሥራው በቤተሰብ ጉልበት እንደሚሠራ ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ሰንጠረዥ .. የ1 ቀን የእንቁላል ጣይ ዝርያ ጫጩቶችን በማሳደግ የ2 ወር ዕድሜ ጫጩት የማምረት የአዋጭነት ስሌት

ተ.ቁ     የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣ የማከማቻ/store)ካ.ሜ905,000.00   450,000.00
2ማግለያካ.ሜ6 5,000.00     30,000.00
3መጠጫቁጥር20230.00      4,600.00
4መመገቢያቁጥር20290.00      5,800.00
5መከለያ/ግርዶሽሜትር60 50.00      3,000.00
6ባለ144 ሻማ/W ኢንፍራ-ሬድ አምፑ ብሩደርቁጥር21,500.00      3,000.00
7አካፋቁጥር2480.00        960.00
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር1190.00         190.00
9የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊ.)ቁጥር116,000.00     16,000.00
10የእርባታ አልባሳት (ቦት ጫማ)ቁጥር2    360.00         720.00
11የእርባታ አልባሳት (ቱታ)ቁጥር2    780.00       1,560.00
12መንቁር መቁረጫ (ዲቢከር)ቁጥር18,500.00      8,500.00
13መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11,600.00       1,600.00
14የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር4  3,200.00     12,800.00
15ተንጠልጣይ ሚዛን (በኤሌክትሪክ የሚሰራ) ቁጥር1 4,000.00      4,000.00
16የክትባት ማጓጓዣ (Ice Box with Ice Bag: 10lit.)ቁጥር1 2,800.00      2,800.00
17የጫጩት መከተቢያ (Eye Dropper)ቁጥር1    900.00        900.00
18መከተቢያ (የክንፍ መብጫ-Double Needle Applicator)ቁጥር1    800.00        800.00
19ማስክ/ጎግል (የአይን መከላከያ)ቁጥር1  150.00         150.00
20ማስክ/ጎግል (የአፈና የአፍንጫ)ቁጥር1  3,200.00      3,200.00
21ጋሪ /Wheel-Barrow/ (ቱርክ ሰራሽ)ቁጥር1 6,000.00      6,000.00
22የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜል (የፕላስቲክ፣ ባ120 ሊትር)ቁጥር1  1,400.00       1,400.00
 ጠቅላላ ድምር557,980.00

ሰንጠረዥ .. ሰንጠረዥ 2 የቋሚ እቃ የአገልግሎት ዘመናት ተቀናናሽ ወጪ

ተ.ቁ የግብዓት ዓይነትመለኪያጠቅላላ ዋጋየአገልግሎት ዘመንየ1 ዓመት ተቀናናሽ ወጪየ1 ዙር ተቀናናሽ ወጪ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣ የማከማቻ/store)ካ.ሜ450,000.0020 22,500.00 5,625.00
2ማግለያካ.ሜ 30,000.0020 1,500.00 375.00
3መጠጫቁጥር   4,600.003     1,533.33            383.33
4መመገቢያቁጥር   5,800.005         1,160.00           290.00
5መከለያ/ግርዶሽሜትር   3,000.001       3,000.00            750.00
6ባለ144 ሻማ/ ኢንፍራ-ሬድ አምፑ ብሩደርቁጥር   3,000.005          600.00            150.00
7አካፋቁጥር     960.005          192.00             48.00
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር      190.005           38.00               9.50
9የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊ.)ቁጥር  16,000.0010        1,600.00           400.00
10የእርባታ አልባሳት (ቦት ጫማ)ቁጥር     720.002          360.00             90.00
11የእርባታ አልባሳት (ቱታ)ቁጥር   1,560.002          780.00            195.00
12መንቁር መቁረጫ (ዲቢከር)ቁጥር   8,500.0015         566.67             141.67
13መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር   1,600.0010          160.00             40.00
14የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር  12,800.0010        1,280.00            320.00
15ተንጠልጣይ ሚዛን (በኤሌክትሪክ የሚሰራ) ቁጥር   4,000.0010          400.00            100.00
16የክትባት ማጓጓዣ (Ice Box with Ice Bag: 10lit.)ቁጥር   2,800.0010280.00             70.00
17የጫጩት መከተቢያ (Eye Dropper)ቁጥር     900.005          180.00             45.00
18መከተቢያ (የክንፍ መብጫ-Double Needle Applicator)ቁጥር     800.005          160.00             40.00
19ማስክ/ጎግል (የአይን መከላከያ)ቁጥር      150.003           50.00              12.50
20ማስክ/ጎግል (የአፈና የአፍንጫ)ቁጥር   3,200.003        1,066.67           266.67
21ጋሪ /Wheel-Barrow/ቁጥር   6,000.0010          600.00            150.00
22የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜል (የፕላስቲክ፣ ባ120 ሊትር)ቁጥር   1,400.005          280.00             70.00
 ጠቅላላ ድምር557,980.0038,286.679,571.67

ሰንጠረዥ 3 የስራ ማስኬጃ ወጪ

ተ.ቁየግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ የ1 ዙር ወጪ ጠቅላላ የ1 ዓመት ወጪ
1ጫጩቶችቁጥር100073 73,000.00292,000.00
2መኖ (Feed)ኪ.ግ200037 74,000.00 96,000.00
3ክትባትዶዝ11,0000.6 6,600.00 26,400.00
4መድሃኒትና ቫይታሚንበግምት5 5,000.00 20,000.00
5የወለል ጉዝጓዝቤል9120 1,080.00 4,320.00
6ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፈክታንት)በግምት2000 2,000.00 8,000.00
7የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪለአንድ ዙር/በግምት –3000 3,000.00 12,000.00
8ንዑስ ድምር    164,680.00658,720.00
 የአገልግሎት ተቀናሽለምፕ ሰም  38,286.679,571.67
 ድምር   202,966.67668,291.67
 መጠባባቂያ (5%)    10,148.33 33,414.58
 ጠቅላላ ድምር    213,115.00 701,706.25

ሰንጠረዥ 4 የገቢ ስሌት

ተ.ቁየገቢ ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ የ1 ዙር የገቢ ስሌትጠቅላላ የ1 ዓመት የገቢ ስሌት
1የ60 ቀን ጫጩት ሽያጭቁጥር950250237,500.00950,000.00
2ከዶሮ ኩስ ሽያጭኩ/ል5030015,000.0060,000.00
ጠቅላላ ገቢብር  252,500.001,010,000.00
ወጪብር  213,115.00701,706.25
የተጣራ ትርፍብር  39,385.00308,293.75

ማጠቃለያ፡-

  • በግል/በማህበር ተደራጀተው የሚያሳድጉ አሳዳጊዎች በ1 ዙር (በ60 ቀን) የሚያገኙት የተጣራ ትርፍ 39,385.00 ብር ወይም በዓመት (በ4 ዙር) 308,293.75 ብር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • Retun on Investment/ROI (ጠቅላላ ገቢ ሲቅነስ ጠቅላል ወጪ ሲካፍል ጠቅላል ወጪ) (1,010,000.00 – 701,706.25/701,706.25 x 100%) = 43.93%
  • በጫጩት ማሳደግ ንዑስ ዘርፍ የተሰማራ አንድ አርቢ ላወጣው/Investment/ላደረገው በያንዳዱ ብር 701,706.25 የማትረፍ አቅሙ ብር 43.93 ያተርፋል ማለት ነወ፡፡
  • ለእርባታ የዶሮ ቤት ገንብቶ፣ በዓመት አንድ ዙር ብቻ ጫጩት ማሳደግ፣ የቤቱና ሌሎቸ ቋሚ የእርባታ ቁሳቁሶች ተቀናሽ ብዙ ስለሚሆን፣ የሚገኘው የተጣራ ትርፍ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ሰለሆነም ሁኔታዎችን በማመቻቸት ቢንስ ሁለት ዙርና ከዚያ በላይ እንዲያሳድጉ ማገዝያ ያስፈልጋል፡፡ 
  • በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡

ታሳቢዎች፡-

  • የሞት መጠን 5% ታሳቢ ተወስዷል ስለሆነም 1000X10% = 950 የ45 ቀን ጫጩቶች ያድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡
  • መጠባበቂያ ከተቅላላ ወጪ 5% ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ሰንጠረዥ .. የ1 ቀን ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩት በማሳደግ የ2 ወር ዕድሜ ጫጩት የማምረት የአዋጭነት ስሌት

ተ.ቁ     የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣ የማከማቻ/store)ካ.ሜ905,000.00   450,000.00
2ማግለያካ.ሜ6 5,000.00     30,000.00
3መጠጫቁጥር20230.00      4,600.00
4መመገቢያቁጥር20290.00      5,800.00
5መከለያ/ግርዶሽሜትር60 50.00      3,000.00
6ባለ144 ሻማ/W ኢንፍራ-ሬድ አምፑ ብሩደርቁጥር21,500.00      3,000.00
7አካፋቁጥር2480.00        960.00
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር1190.00         190.00
9የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊ.)ቁጥር116,000.00     16,000.00
10የእርባታ አልባሳት (ቦት ጫማ)ቁጥር2    360.00         720.00
11የእርባታ አልባሳት (ቱታ)ቁጥር2    780.00       1,560.00
12መንቁር መቁረጫ (ዲቢከር)ቁጥር18,500.00      8,500.00
13መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11,600.00       1,600.00
14የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር4  3,200.00     12,800.00
15ተንጠልጣይ ሚዛን (በኤሌክትሪክ የሚሰራ) ቁጥር1 4,000.00      4,000.00
16የክትባት ማጓጓዣ (Ice Box with Ice Bag: 10lit.)ቁጥር1 2,800.00      2,800.00
17የጫጩት መከተቢያ (Eye Dropper)ቁጥር1    900.00        900.00
18መከተቢያ (የክንፍ መብጫ-Double Needle Applicator)ቁጥር1    800.00        800.00
19ማስክ/ጎግል (የአይን መከላከያ)ቁጥር1  150.00         150.00
20ማስክ/ጎግል (የአፈና የአፍንጫ)ቁጥር1  3,200.00      3,200.00
21ጋሪ /Wheel-Barrow/ (ቱርክ ሰራሽ)ቁጥር1 6,000.00      6,000.00
22የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜል (የፕላስቲክ፣ ባ120 ሊትር)ቁጥር1  1,400.00       1,400.00
 ጠቅላላ ድምር557,980.00

 ሰንጠረዥ 2. ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶችን በማሳደግ የ2 ወር ዕድሜ ጫጩት የማምረት የቋሚ ዕቃ የአገልግሎት ዘመናት ተቀናናሽ ወጪ

ተ.ቁ የግብዓት ዓይነትመለኪያጠቅላላ ዋጋየአገልግሎት ዘመንየ1 ዓመት ተቀናናሽ ወጪየ1 ዙር ተቀናናሽ ወጪ
1የእርባታ ቤት (የሰራተኛ ማረፊያ፣ የማከማቻ/store)ካ.ሜ450,000.0020 22,500.00 5,625.00
2ማግለያካ.ሜ 30,000.0020 1,500.00 375.00
3መጠጫቁጥር   4,600.003     1,533.33            383.33
4መመገቢያቁጥር   5,800.005         1,160.00           290.00
5መከለያ/ግርዶሽሜትር   3,000.001       3,000.00            750.00
6ባለ144 ሻማ/ ኢንፍራ-ሬድ አምፑ ብሩደርቁጥር   3,000.005          600.00            150.00
7አካፋቁጥር     960.005          192.00             48.00
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር      190.005           38.00               9.50
9የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊ.)ቁጥር  16,000.0010        1,600.00           400.00
10የእርባታ አልባሳት (ቦት ጫማ)ቁጥር     720.002          360.00             90.00
11የእርባታ አልባሳት (ቱታ)ቁጥር   1,560.002          780.00            195.00
12መንቁር መቁረጫ (ዲቢከር)ቁጥር   8,500.0015         566.67             141.67
13መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር   1,600.0010          160.00             40.00
14የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር  12,800.0010        1,280.00            320.00
15ተንጠልጣይ ሚዛን (በኤሌክትሪክ የሚሰራ) ቁጥር   4,000.0010          400.00            100.00
16የክትባት ማጓጓዣ (Ice Box with Ice Bag: 10lit.)ቁጥር   2,800.0010280.00             70.00
17የጫጩት መከተቢያ (Eye Dropper)ቁጥር     900.005          180.00             45.00
18መከተቢያ (የክንፍ መብጫ-Double Needle Applicator)ቁጥር     800.005          160.00             40.00
19ማስክ/ጎግል (የአይን መከላከያ)ቁጥር      150.003           50.00              12.50
20ማስክ/ጎግል (የአፈና የአፍንጫ)ቁጥር   3,200.003        1,066.67           266.67
21ጋሪ /Wheel-Barrow/ቁጥር   6,000.0010          600.00            150.00
22የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜል (የፕላስቲክ፣ ባ120 ሊትር)ቁጥር   1,400.005          280.00             70.00
 ጠቅላላ ድምር557,980.0038,286.679,571.67

ሰንጠረዥ 3 ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶችን በማሳደግ የ2 ወር ዕድሜ ጫጩት የማምረት የስራ ማስኬጃወጪ

.የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ 1 ዙር ወጪ ጠቅላላ 1 ዓመት ወጪ
1የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ የ1 ዙር ወጪ ጠቅላላ የ1 ዓመት ወጪ
2ጫጩቶችቁጥር100050 50,000.00200,000.00
3መኖ (Feed)ኪ.ግ200037 74,000.00296,000.00
4ክትባትዶዝ11,0000.6 6,600.00 26,400.00
5መድሃኒትና ቫይታሚንበግምት5 5,000.00 20,000.00
6የወለል ጉዝጓዝቤል9120 1,080.00 4,320.00
7ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፈክታንት)በግምት2000 2,000.00 8,000.00
8የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪለአንድ ዙር/በግምት –3000 3,000.00 12,000.00
 ንዑስ ድምር    141,680.00566,720.00
 የአገልግሎት ተቀናሽለምፕ ሰም  38,286.679,571.67
 ድምር    179,966.67576,291.67
 መጠባባቂያ (5%)    8,998.33 28,814.58
 ጠቅላላ ድምር    188,965.00605,106.25

ሰንጠረዥ 4 ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያ ጫጩቶችን በማሳደግ የ2 ወር ዕድሜ ጫጩት የማምረት የገቢ ስሌት

ተ.ቁየገቢ ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ የ1 ዙር የገቢ ስሌትጠቅላላ የ1 ዓመት የገቢ ስሌት
1የ60 ቀን ጫጩት ሽያጭቁጥር950200190,000.00760,000.00
2ከዶሮ ኩስ ሽያጭኩ/ል5030015,000.0060,000.00
3ጠቅላላ ገቢብር  205,000.00820,000.00
ወጪብር  188,965.00605,106.25
የተጣራ ትርፍብር  16,035.00214,893.75

ማጠቃለያ፡-

  • በግል/በማህበር ተደራጀተው የሚያሳድጉ አሳዳጊዎች በ1አንድ ዙር (በ60 ቀን) የሚያገኙት የተጣራ ትርፍ 16,035.00 ብር ወይም በዓመት (በ4 ዙር) 214,893.75 ብር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • Retun on Investment/ROI (ጠቅላላ ገቢ ሲቅነስ ከጠቅላል ወጪ ሲካፍል ለጠቅላል ወጪ) (820,000.00605,106.25/605,106.25 x 100%) = 35.51%
  • በጫጩት ማሳደግ ንዑስ ዘርፍ የተሰማራ አንድ አርቢ ላወጣው/Investment/ላደረገው በያንዳዱ ብር 701,706.25 የማትረፍ አቅሙ ብር 35.51 ያተርፋል ማለት ነወ፡፡
  • ለእርባታ የዶሮ ቤት ገንብቶ፣ በዓመት አንድ ዙር ብቻ ጫጩት ማሳደግ፣ የቤቱና ሌሎቸ ቋሚ የእርባታ ቁሳቁሶች ተቀናሽ ብዙ ስለሚሆን፣ የሚገኘው የተጣራ ትርፍ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ሰለሆነም ሁኔታዎችን በማመቻቸት ቢንስ ሁለት ዙርና ከዚያ በላይ እንዲያሳድጉ ማገዝያ ያስፈልጋል፡፡ 
  • በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡

ታሳቢዎች፡

  • የሞት መጠን 5% ታሳቢ ተወስዷል ስለሆነም 1000X10% = 950 የ45 ቀን ጫጩቶች ያድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡
  • መጠባበቂያ ከተቅላላ ወጪ 5% ታሳቢ ተደርጓል፡፡

4.   የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

አነስተኛና መካከለኛ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

ይህ ፓኬጅ ከፍተኛ የእንቁላል ምርት የሚሰጡ ዝርያ ዶሮዎች ላይ ተመሥርቶ በዋነኛነት የመብል እንቁላል ለገበያ በማቅረብ ገቢ ለማግኘትና የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃን በማሻሻል የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንዲቻል ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ፓኬጅ አነስተኛ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ከ500 ቄብ የሚጀምር ሲሆን መካከለኛ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ደግሞ ከ 1000 በላይ ያሉትን ይሆናል፡፡

ዝርዝር የፓኬጁ አላማ፡-

  • የዶሮ ስጋና እንቁላል ምርትን በመጨመር የህብረተሰቡን የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲሁም ድህነትን በመቀነስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማስቻል፣
  •  ጤናማ ዜጋን በማፍራት በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡን የፕሮቲን ፍላጎት በማሟላትና አመጋገቡም በህብረተሰብ ደረጃ በቀላሉ መዘጋጀት የሚችል እንዲሆን በሰርቶ ማሳያ መልክ በማስተማር የህብረተሰቡን በተለይም የእናቶችና ህጻናትን የስነ ምግብ ይዘት ማሻሻል፣
  •  የአምራቹን የገቢ ምንጭ አማራጮችን በማስፋት የህብረተሰቡን ገቢ በማሳደግ ኑሮው እንዲሻሻል ማገዝ፣
  •  ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ለማህበራዊ ችግሮች መቀረፍ አስተዋጽኦ ማድረግ፣
  • አምራቹንና ግብዓት አቅራቢዎችን በማስተሳሰር የተቀናጀ የዶሮ እርባታ ስርዓት መዘርጋትና ከመንግስት ብቻ የሚጠበቀውን ድጋፍ መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
  • አርቢው ምርቱን እሴት በመጨመር እንቁላልና የተዘጋጀ የዶሮ ሥጋ በፍሪጅ አቆይቶ በጥንቃቄ በመያዝ የገበያ መቀዛቀዝ በሚኖርባቸው የጾም ወራት ካለፉ በኋላ መሸጥ ይኖርበታል፡፡

የፓኬጁ ጥንቅሮች 

የግብዓት ፍላጐት በምሳሌነት ለአነስተኛ 500 የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ለእንቁላል ምርት የቀረበ

ተ.ቁ    የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ ፤ካ.ሜ1005000 500,000
2ማግለያካ.ሜ45000 20,000
3የዕንቁላል መጣያቁጥር100200 20,000
4የዕንቁላል ማጓጓዣ ትሪቁጥር25050 12,500
5መጠጫቁጥር20260 5,200
6መመገቢያቁጥር20260 5,200
7አካፋቁጥር2170 340
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120 120
9የዉሃ ማጠራቀሚያ(ባለ1000 ሊትር)ቁጥር14500 4,500
10የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር2600 1,200
13አምፑል (60W)ቁጥር550 250
14መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11000 1,000
15የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር23200 6,400
16የእጅ ጋሪቁጥር1      3500 3,500
17ቄቦችቁጥር500250 125,000
18መኖ (Feed)- ከትራንስፖርት ጋርኪ.ግ30,45039 1,187,550
19የመኖ ትራንስፖርትብር57,330
20ክትባት/ቄብቁጥር5004 2,000
21 መድሃኒትና ቫይታሚንቁጥር50010 5,000
22ጉዝጓዝኩ/ል30100 3,000
23ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፌክታንት)ሊትር6150 900
24የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪወር192500 47,500
25መዝገብቁጥር1120 120

የግብዓት ፍላጐት በምሳሌነት ለመካከለኛ 1000 የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ለእንቁላል ምርት የቀረበ

ተ.ቁ   መለኪያብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
  የግብዓት ዓይነት    
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ ፤ካ.ሜ200 5,000 1,000,000
2ማግለያካ.ሜ8 5,000 40,000
3የዕንቁላል መጣያቁጥር200 200 40,000
4የዕንቁላል ማጓጓዣ ትሪቁጥር500 50 25,000
5መጠጫቁጥር40 260 10,400
6መመገቢያቁጥር40 260 10,400
7አካፋቁጥር4 170 680
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር2 120 240
9የዉሃ ማጠራቀሚያ(ባለ1000 ሊትር)ቁጥር2 4,500 9,000
10የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር4 600 2,400
13አምፑል (60W)ቁጥር10 50 500
14መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር2 1,000 2,000
15የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር4 3,200 12,800
16የእጅ ጋሪቁጥር2 3,500 7,000
17ቄቦችቁጥር1000 250 250,000
18መኖ (Feed)ኪ.ግ60900 39 2,375,100
19የመኖ ትራንስፖርትብር0 2 114,660
20ክትባት/ቄብቁጥር1000 4 4,000
21 መድሃኒትና ቫይታሚንቁጥር1000 10 10,000
22ጉዝጓዝኩ/ል60 100 6,000
23ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፌክታንት)ሊትር12 150 1,800
24የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪወር38 2,500 95,000
25መዝገብቁጥር2 120 240

4.1.     ለእንቁላል ዶሮ እርባታ ፓኬጅ ማስፈፀሚያ ስልቶች

የዕንቁላል ምርት ላይ ያተኮረ የእንቁላል ዶሮ እርባታ ሆኖ ከለማ እንቁላል፣ ከጫጩት እንዲሁም እንቁላል ሊጥሉ ከደረሱ ቄብ ዶሮዎች ሊጀምር ይችላል፡፡ እያንዳንዱ አማራጭ እንደ እርባታው ተጨባጭ ሁኔታ የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት ሊኖረው ይችላል፡፡ ለዚህ ፓኬጅ ግን በቄብ ዶሮ መጀመር የተሻለ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል፡፡

በቄብ ዶሮ መጀመር፡ጫጩቶችን አሳድገው የ45ቀን፣ የሁለትና የሶስት ወር ዕድሜ ያሉ ቄቦችን ከሚሸጡ አሳዳጊዎች/አርቢዎች ገዝቶ መጀመር ይቻላል፡፡

የእንቁላል ጣይ ቄቦች ዝርያና ምንጭ

የሀገራችን የአብዛኛው የአካባቢውን የአየር ፀባይ መቋቋም የሚችሉ ከፍተኛ የእንቁላል ምርት የሚሰጡ ዲቃላ (hybrid) የተሻሻሉ ቄብ የእንቁላል ዝርያ ዶሮዎች መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በብዛት አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉት ቦቫንስ ብራውን (Bovans Brown) ፤ ቦቫንስ ዋይት (Bovans White) ሎህማንስ ብራውን (Lohmanns Brown) ፤ ሎህማንስ ዋይት (Lohmanns White) ፤ ቴትራ እና ኋይት ሌግ ሆርን (Whit Leg Horne)  ሲሆኑ እነዚህንና ሌሎች አዳዲስ የቄብ ዝርያ ዶሮዎች ምንጭ በአሁኑ ሰዓት ጫጩት ከሚያሳድጉ የግልና የመንግስት እርባታ ማዕከላት ይሆናል፡፡ የሚቀርቡት ቄብ ዶሮዎች በክትባት ካላንደሩ መሠረት አስፈላጊውን ክትባት ያገኙ መሆን አለባቸው፡፡

የቄብ ዶሮች የመኖ ይዘትና አመጋገብ

ከ8-20 ሣምንት ባለው ዕድሜ የቄብ ዶሮዎች አመጋገብ ለቀጣዩ የእንቁላል ምርት ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡ ቄቦች ለዝርያቸው የሚመጥን ዕድገት ኖሯቸው በተገቢው ወቅት የዕንቁላል መጣል ተግባራቸውን መጀመር አለባቸው፡፡ በዚህ ዕድሜ ከጫጩትነት ጊዜ የፕሮቲን ፍላጐት ይቀንሳል፡፡ በዚህ ወቅት የፕሮቲን ፍላጐት ከ15-16% ይሆናል፡፡ ከዚህ የበለጠ የፕሮቲን አቅርቦት የመኖ ወጪን ከመጨመሩ በላይ ቄቦች ከሚፈለገው የዕድገት መጠን በላይ በማደግ የመራቢያ አካላቸው ሳይዳብር ዕንቁላል መጣል  እንዲጀምሩ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የዶሮቹን የምርት ዘመን ውጤታማነት ይቀንሰዋል፡፡ ኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብን በተመለከተ ከ8-14 ሣምንት ዕድሜ 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ መኖ ሲያስፈልግ ከ14-20 ሣምንት ባለው ዕድሜ ግን የስብ ክምችትን ለመከላከል ወደ 2700 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ መቀነስ ይኖርበታል፡፡ ለቄብ ዶሮች (ከ8-20 ሳምንት) እለታዊ የመኖ ፍጆታ በአማካኝ 65 ግራም መኖ በቀን መመገብ አለባቸው፡፡

የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የመኖ ይዘትና አመጋገብ

እንቁላ ጣይ ዶሮዎች ዕንቁላል መጣል ከሚጀምሩበት ጥቂት ቀደም ብሎ የመኖ ለውጥ ሂደት መጀመር አለበት፡፡ በዚህ ወቅት ከታዳጊዎች መኖ ወደ እንቁላል ጣይ መኖ ለውጥ ይደረጋል፡፡ የዕንቁላል ምርት ፍላጐትን ለማርካት የካልሲየም አቅርቦት መጨመር አለበት፡፡ ይህም በመኖ ውስጥ ከሚደባለቀው በተጨማሪ በተለየ መመገቢያም ከፍተኛ የካልሲየም ይዘት ያለው ያልደቀቀ በዛ ያለ በሀ/የኖራ ድንጋይ ለእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሊቀመጥላቸው ይገባል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ 2850 ኪሎ ካሎሪ በኪ.ግ. መኖ የኃይል ምንጭ ሊኖረው ይገባል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የፕሮቲን ፍላጐት ከእንቁላል ምርት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእንቁላል መጣያ ወቅት ያለውን አማካይ ፍላጐት ለማርካት የእንቁላል ጣይ መኖ 16.5% ፕሮቲን ሊኖረው ይገባል፡፡

ከላይ የተዘረዘረውን የንጥረ መኖ ይዘት (nutrient) ፍላጐት የሚያሟላ የተደባለቀ መኖ ከመኖ ማደራጃዎች መግዛት ወይም ከተቀመጡት አማራጭ ቀመሮች ላይ በመመሥረት አርቢው በአካባቢው ሊያገኛቸው ከሚችል የመኖ ዓይነቶች ራሱ አደባልቆ ሊጠቀም ይችላል፡፡

4.2.     የእንቁላል ዝርያ ዶሮዎች አማራጭ የመኖ ቀመር

የመኖ ጥሬ ዕቃ ጫጩት (0-8 ሣምንት ዕድሜ)ታዳጋ (8-18 ሣምንት)እንቁላል ጣይ (-18 ሣምንት)
12345678912345123456789
የተከካ በቆሎ5050503630254744304842504232403740454840253651
ፉሩሽኬሎ 25292918192791020231016221832232610142010
የተፈጨ ሥጋና አጥንት 444610107559585.5107
የኑግ ፋጉሎ 2035151324213533373018.51815112010
የጐመን ዘር ፋጉሎ 16
የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ 16
ጨው<0.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.5
የቪታሚንና ማዕድን ድብልቅ*0.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.5
የተከካ የኖራ ድንጋይ 112211213.54.53333
የተፈጨ አጥንት 322122453.53.5
ማሽላ 2523142153016
የቢራ አተላ 1515
የቢራ ብቅል ተረፈ ምርት 10
አልፋ አልፋ ቅጠል 55555544
የለውዝ ፋጉሎ 2020151510
የተፈጨ ሥጋ 44443.54.5
የተፈጨ ዓሣ 333333
ገብስ10101010

የመኖ ብክነትን መከላከል

በማንኛውም ዓይነት የዶሮ እርባታ ውስጥ እስከ 75% ድረስ የሚደርሰውን ከፍተኛ ወጪ የሚይዘው የመኖ ወጪ ነው፡፡ በመሆኑም መኖን ከብክነት በመከላከል በአግባቡ መጠቀምና ለዶሮዎች እንዲውል ማድረግ እርባታውን ትርፋማ ከሚያደርጉት ስልቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ የመኖ ብክነት በተለያዩ መንገዶች በተለይም በሚዘጋጅበት፤ በሚጓጓዝበት፤ በሚከማችበት፤ ለዶሮዎች በሚሰጥበት ወቅትና ዶሮዎችም ሲመገቡ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡

በመሆኑም በመኖ ብክነት ምክንያት የሚመጣ አላስፈላጊ ወጪን ለመቀነስ በመመገቢያዎች ውስጥ ያለውን የመኖ መጠን በመቀነስ ሲያስፈልግ እየተከታተሉ መጨመር ይገባል፡፡ መመገቢያዎች 2/3ኛ ከተሞሉ ወደ 10% የሚጠጋ መኖ ሊባክን ይችላል፡፡ ይህን መጠን ወደ 1/3ኛ ዝቅ ማድረግ ብክነቱን ወደ 1% ያወርደዋል፡፡ ቄቦች እያደጉ ሲሄዱ በየጊዜው ከመካከላቸው አማካይ ዕድገት ባለው የቄቦች የጀርባ ከፍታ መጠን የመመገቢያውን ከፍታ መጨመር ያስፈልጋል፡፡

የውሃ አቅርቦት

ውሃ ከንጥረ ምግቦች ተርታ ባይመደብም እጅግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ዶሮዎች የሚያሥፈልጋቸውን የውሃ መጠን እንደ አካባቢው የሙቀት መጠን፤ የመኖ ፍጆታ፤ የውሃው ሙቀት፤ የእንቅስቃሴና የምርት መጠን ወዘተ ይለያያል፡፡ ለዶሮዎች የምንሰጣቸው ውሃ በተቻለ መጠን ንጹህና ከብክለት የጸዳ መሆን አለበት፡፡

በአጠቃላይ የውሃ እጥረት በዶሮዎች ላይ የሚከተሉትን ችግሮች ያስከትላል፡፡

  • የመኖ አለመፈጨትና አለመወሃድ፤
  • የእንቁላል ምርት መቀነስ በመጨረሻም የእንቁላል ምርት ማቆም፤
  • የሰውነት ሙቀት መጨመርና በመጨረሻም መሞት ናቸው፡፡

የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ጤና አጠባበቅና ሥነ-ህይወት ጥበቃ

የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች

ክትባት (Vaccination)          

ከጫጩት እስከ ቄብ ዕድሜ ክልል ውስጥ (ከአንድ ቀን እስከ ሶስት ወር) በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ውስጥ አሉ የሚባሉ የዶሮ በሽታዎችን እንደ ማሬክስ፤ ኒውካስትል፤ ጉምቦሮ ፋዎል ታይፎይድና ፋዎል ፖክስ የመሳሰሉትን የወሰዱ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቄብነት ወደ እርባታው ከገቡ በኃላ የሚሰጣቸው ክትባቶች በአካባቢው የሚገኙ የእንስሳት ሀኪሞችን በማማከር ማስከተብ ያስፈልጋል፡፡ የዶሮዎች የክትባት ፕሮግራም በክትባት አምራች ካምፓኒውና በእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በሚወጣው የክትባት መርሀ ግብር መሰረት እንደ አስፈላጊነቱ የሚፈጸም ሆኖ በፈንግል በሽታ ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሠንጠረዥ፡- 2 በክትባት አሰጣጥ ወቅት ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን ይመልከቱ፡፡

  የዶሮ እድሜ  የክትባት ዓይነት  የክትባት አሰጣጥ ዘዴ
     በ28ሳምንትNCD (Lasota)በዓይን ጠብታ እና በመጠጥ ውሃ
በ 32ኛ ሳምንትNCD (Lasota)በዓይን ጠብታ እና በመጠጥ ውሃ
በ 48ኛ ሳምንትNCD (Lasota)በዓይን ጠብታ እና በመጠጥ ውሃ
በ 64ኛ ሳምንትNCD (Lasota)በዓይን ጠብታ እና በመጠጥ ውሃ

በሽታን በመድሃኒት መከላከል

ዶሮዎችን በሽታ ከያዛቸው በኋላ ከማከም ይልቅ በሽታው ከመከሰቱ በፊት መከላከል የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ የዶሮዎች በሽታ ለመከላከል ጥራቱንና ወቅቱን የጠበቀ የክትባት አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የበሽታ ፍንዳታ ይከሰታል ተብሎ የሚጠረጠርባቸው ወቅቶች (Disease outbreak) ላይ በባክቴርያ (Bacteria) አማካኝነት ለሚመጡ በሽታዎች አንቲ ባዮቲክ (Antibiotic) እንደነ ዶክሲቪቶ (Doxyveto)፤ አሞክሲቪቶ (Amoxyveto) እና ኮሊቪቶ (Coliveto) የመሳሰሉትን እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በኮክሲዲዮሲስ (Coccidiosis) አማካኝነት ለሚመጣ በሽታ የፀረ ኮክሲዲዮሲስ መድኃኒት (Anti-Coccidiosis Drug) አምፕሮሊየም ፕሪቬንቲቭ ዶዝ (Amprolium Preventive Dose) በየ15 ቀን ልዩነት ቢሰጥ ጥሩ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ጥንቃቄ በኋላ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች አስፈላጊውን ህክምና በባለሙያ እንዲሰጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በእርባታ ደረጃ በሽታን ለመከላከል የሚከተሉትን ዘዴዎች መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ዶሮዎችን ለይቶ ማርባት

  • በእርባታው ቤት ውስጥ አንድ ዓይነት ዕድሜና አንድ ዓይነት ዝርያ ያላቸውን ዶሮዎች ማቆየት ተገቢ ነው፣
  •  በአንድ እርባታ ውስጥ ቢቻል በቤቶች መካከል ቢያንስ የ12 ሜትር ርቀት ሊኖር ይገባል፤
  • እርባታው ከመኖሪያ ቤት፣ከመንገድና ከሌሎች የእርባታ ጣቢያዎች ቢያንስ 300 ሜትር መራቅ አለበት፤

 በሽታን ለመከላከል የሚያግዝ የቤት አሠራር መጠቀም

  • የእርባታው ቤት ሲሰራ ወፎችን ሙሉ በሙሉ የሚከላከል መሆን አለበት፡፡
  • የእርባታው ቤት መግቢያ በር ላይ ሰው ረግጦት የሚገባ የፀረ-ተዋስያን መድሃኒት ዲስ ኢንፌክታንት (Disinfectants) ጐድጐድ ባለ ሥፍራ ላይ መኖር አለበት፡፡  
  • የእርባታው ቤት በቂ የአየር እንቅስቃሴ እንዲኖረው ተደርጐ መሠራት አለበት፡፡
  • የእርባታው ቤት በተለይ ወለሉ በቀላሉ ሊፀዳ የሚችል መሆን አለበት፡፡ 

ሠራተኞች ሊያደርጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

  • ከዶሮዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠራተኞች የዶሮ ጤና አጠባበቅ ጥንቃቄዎች አስፈላጊነት የሥራ ላይ ሥልጠና መሰጠት አለበት፡፡
  • ሠራተኞች እንደ እርባታው ደረጃ የሥራ ልብስ /የራስ መሸፈኛ፤ ቱታና ቦት ጫማዎች ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 
  • የውጪ ጎብኚዎች እርባታው ውስጥ መግባት የለባቸውም፡፡ መግባት ካለባቸውም በእርባታ ማዕከሉ የተዘጋጀውን የስራ ልብስ ለብሰው መግባት ኣለባቸው፡፡ 
  • የእርባታው ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ቢቻል የራሳቸው የዶሮ እርባታ የሌላቸው መሆን አለባቸው፡፡

የንፅህና አጠባበቅና ቁጥጥር 

  • ከዶሮዎች ቤት አካባቢ ጢሻ፣ የቆሻሻ ክምችት፤ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቁሳቁስ ክምችት ለአይጦችና ሌሎች በሽታ አስተላላፊዎች መደበቂያና መራቢያ ሊሆን ስለሚችል መወገድና መጽዳት አለበት፤ 
  • ቀደም ሲል ጥቅም ላይ የዋለ የዶሮ ቤት ጉዝጓዝ ከዶሮዎች ቤት ሲወገድ ቢያንስ 300 ሜትር ያህል መራቅ አለበት፤ 
  • የሞቱ ወይም ታመው የመዳን ተስፋ የሌላቸው ዶሮዎች ለሌሎች የችግር ምንጭ ስለሚሆኑ ከዶሮዎች ቤት ርቆ የተቆፈረ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መጣልና ማቃጠል ወይም መቅበር ያስፈልጋል፤
  • አዲስ ዶሮዎች ከመግባታቸው በፊት ቤቱ /ከቁሳቁስ ጭምር/ በሚገባ ፀድቶና ፀረ-ተባይ ኬሚካል ተረጭቶ ለሁለት ሣምንታት ያህል ባዶውን መቆየት አለበት፡፡ 
  • ዶሮዎች የሚያድሩበትን አካባቢ፣ መጠጫዎችና መመገቢያዎች በየጊዜው ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡

    የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች መጠለያ አሰራር

     የዶሮ ቤት አሰራር ቅድመ ሁኔታዎች

የዶሮ ቤት ዶሮዎችን ከፀሀይ፤ ከብርድ፤ ከዝናብ፤ ከአውሬና ከመሳሰሉት ለመጠበቅ በተለያዩ ቁሳቁሶችና ቅርጾች የሚሰራ ነው፡፡ የዶሮ ቤት ሲሰራ ጥንቃቄ ካልተደረገ ዶሮዎች በአግባቡ አያድጉም፤ የሚገኘው ምርትም ይቀንሳል፡፡ ማንኛውም የዶሮ ቤት አሠራር እንደሚረቡት ዶሮዎች መጠን ቢለያይም  ለቄቦች እና ለዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች በሚያስፈልጋቸው የቦታ መጠን መዘጋጀት አለበት፡፡ ዶሮዎችን በተጨናነቀ ሁኔታ ማርባት የተለያዩ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ የሚከሰቱት ችግሮችም፡-

  • የቤቱን ፅዳት ለመቆጣጠር ስለሚያስቸግር ዶሮዎችን ለተለያዩ በሽታዎች ማጋለጥ፣
  • ከሚፈለገው ሙቀት በላይ ከተሰማቸው ምግብና ውሃ በአግባቡ አለመውሰድ፣
  • እርስ በእርሳቸው መነካከስ እና ወደ ዕንቁላል መጣያ ቦታ ለመሄድ እንደልብ መንቀሳቀስ ባለመቻል ዕንቁላል ወለል ላይ እየጣሉ ሰብሮ መጠጣት መልመድ እና የምርት ማባከን ናቸው፡፡

የዶሮዎችን ቤት እንደየሁኔታው በተለያየ ደረጃና ዓይነት ሊሰራ ቢቻልም የሚከተሉትን መሠረታዊ ታሳቢዎች ማሟላት አለበት፡፡

 ሠንጠረዥ 3 የዶሮ ቤት አሰራር ስዕል ይመልከቱ፡፡   

  1. የዶሮ እርባታ ቦታ አመራረጥ (SITE SELECTION OF POULTRY FARM)
  2. ለመኖሪያ ቤት የቀረበ መሆን የለበትም፡፡ ቅርበቱ ለዶሮዎችም ሆነ ለነዋሪዎች ጤናማ ሁኔታን አይፈጥርም፣ እጅግ መራቅም የለበትም ከራቀና በቤተሰብ የሚካሄድ እርባታ ከሆነ ዶሮዎቹም ለመንከባከብ አላስፈላጊ የምልልስ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ርቀቱ ሁለቱን ሁኔታዎችን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡
  3. በቂ የፀሃይ ብርሃን በሚያገኝበት አቅጣጫ መሠራት አለበት፡፡ ይህም በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ዶሮዎች ከሰዓት በኋላ የፀሐይ ብርሀን ይልቅ የጥዋትን ይመርጣሉ፤ ብርሃናማ በሆነ አካባቢም ደስተኛ ናቸው፡፡ ስለዚህ ቤቱ ሲሰራ የጥዋት ፀሃይ ወደ ቤቱ ውስጥ በሚገባበት መልኩ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ መሰራት ይኖርበታል፡፡
  4. ቢቻል በታዳፋት መሬት ላይ ቢሰራ ይመረጣል፡፡ ይህም አካባቢው ውሃ እንዳይተኛበት ይረዳል፡፡ አሸዋማነት ያለው የአፈር ዓይነትም እንዲሁ ውሃ ስለማይቋጥር ከመረሬ አፈር ይልቅ ተመራጭነት አለው፡፡
  5. በዶሮ ቤት አካባቢ ጥላ የሚሰጡ ዛፎች ቢኖሩ በሞቃታማ ወቅት በቤቱ ውስጥ የሚኖረው ሙቀት መጠን ይቀንሳል፡፡ ይህ ግን ቤቱ የፀሐይ ብርሃን እንዳያገኝ የሚከለክል መሆን የለበትም፡፡
  6. የዶሮዎች ቤት አቀማመጥ ኃይለኛ ንፋስ በሚነፍስበት አቅጣጫ መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም ኃይለኛ ንፋስ የሚያገኛቸው ከሆነ ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣሉ፡፡

ለዶሮዎች ምቹ የሆነ የቤት አሰራር፡-

ያልተጨናነቀ፣ በሙቀት ወቅት ውስጡ ቀዝቀዝ ያለ፣ ንፁህ አየር የሚዘዋወርበት፣ በቂ ብርሃን ያለውና መሬቱ እርጥበት የሌለው መሆን አለበት፡፡ ይህ ሁኔታ ከተሟላ የዶሮዎቹ ምርት ከማደጉም በላይ በሽታን መከላከል ይቻላል፡፡

ለአሠራር አመቺ የሆነ ቤት፡-

ቤቱ በአመቺ ቦታ ተሰርቶ በቤቱ ውስጥ ያሉት የተለያዩ መገልገያዎች ለሥራ በሚያመች ሁኔታ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ሠራተኞች በቤቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ ጊዜን በሚቆጥብ መልክ ስራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያመች መሆን አለበት፡፡

ዶሮዎችን ከጥቃት የሚከላከል ቤት፡-

ዶሮዎችን ከሚያጠቁ አውሬዎች፣ ከጥገኛ ተህዋስያን፣ ከዝናብና ከአደገኛ ንፋስ የሚከላከል፣ ዕንቁላል ለሚበሉና ጫጩቶችን ለሚያጠቁ እንደ አይጥ ላሉ አውሬዎች መራባት የማያመች መሆን አለበት፡፡

እንቁላል ጣይ ዶሮዎች የቤት ውስጥ አደረጃጀቶች

የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሙሉ ጊዜያቸውን በቤት ውስጥ የሚያሳልፉበት ተስማሚ የሆነ የተለያየ የቴክኖሎጂ ደረጃ ያላቸው ሁለት ዓይነት ቤቶች (Housing system) መጠቀም ይችላሉ፡፡

  1. ሙሉ ጉዝጓዝ ወለል (Full litter system)
  2. ተደራርቢ ጐጆ (Cage System)

ሙሉ ጉዝጓዝ ወለል (Full litter system)

የሙሉ ጉዝጓዝ ወለል (Full litter system) የቤት ዓይነትበብዛት ሞቃት አካባቢዎች ጥቅም የሚውል ነው፡፡ ጉዝጓዙ በአካባቢ የሚገኝና ርካሽ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ ማንኛውም እርጥበትን ሊመጥ የሚችልና ለዶሮዎች ጤና መርዛማ ያልሆነ ሁሉ ጉዝጓዝ መሆን ይችላል፡፡ ተመራጭ ጉዝጓዝ የእንጨት ፍቅፋቂ ወይም ሠጋቱራ፤ ጭድ እና የቡና ገለባ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በመጀመሪያ ከ 6 እስከ 12 ሳ.ሜ. ያህል እንደ አስፈላጊነቱ በማድረግ መጀመር ይቻላል፡፡ ጉዝጓዙ ምንጊዜም ደረቅ መሆን አለበት፡፡ እርጥብ ጉዝጓዝ ከኮክሲዲዮሲስና ሌሎች በሽታ አምጭ ተህዋስያን እንዲራቡ ምቹ ሁኔታዎችን ስለሚፈጥር ጥንቃቂ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የዶሮ ቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳሶች ማለትም (መመገቢያ፤ መጠጫ፤ ቆጥ/perch የእንቁላል መጣያ ሳጥን (Laying nest) እና ጉዝጓዝ እንደ ሁኔታው ሊኖረው ይገባል፡፡ የዕንቁላል መጣያዉ ልኬታ 30 X 30 X 35 ሣ.ሜ ሲሆን ለስድስት ዶሮ አንድ ዕንቁላል መጣያ ሳጥን (Laying nest) ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የወለል ስፋት ፍላጐት በ1 ካሬ ሜትር ላይ ከ5-7 ዶሮዎች ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የመመገቢያ ፍላጐታቸው በረጅም መመገቢያ (Long feeder) 12ሣ.ሜ. እና በክብ መመገቢያ (Round Feeder) 5ሳ.ሜ ሆኖ የመጠጫ ፍላጐታቸው በረጅም መጠጫ (Long waterer) 2ሣ.ሜ. እና በክብ መጠጫ (Round waterer) 1ሳ.ሜ ለ1 ዶሮ ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀት አለበት፡፡

ሰንጠረዝ1. ¾Êa‹ ¾¨KM eóƒ õLÔƒ

ተራ ቁጥርየዶሮ ዓይነት  ብዛት በካሬ ሜትር  
 አነስተኛ ክብደት ያላቸው የዕንቁላል ዝርያ ሴት ጫጩቶች14  
 መካከለኛ ክብደት ያላቸው የዕንቁላል ዝርያ ሴት ጫጩቶች13
 የሥጋ ዝርያ ሴት ጫጩቶች11
 የሥጋ ዝርያ ወንድ ጫጩቶች9
 የሥጋ ዝርያ ድብልቅ ጾታ ያላቸው ጫጩቶች10
 አነስተኛ ክብደት ያላቸው የዕንቁላል ዝርያ ቄቦች ከ8 እስከ 18 ወር ዕድሜ    12
 – ከ18 እስከ 20 ወር ዕድሜ የዕንቁላል ጣይ ዝርያ7
 መካከለኛ ክብደት ያላቸው የዕንቁላል ዝርያ ቄቦች – ከ8 እስከ 18 ወር ዕድሜ  9
 – ከ18 እስከ 22 ወር ዕድሜ የዕንቁላል ጣይ ዝርያ6  
 የሥጋ ዝርያ ለማዳቀል የሚውሉ ቄቦች4
 የሥጋ ዝርያ ለማዳቀል የሚውሉ አውራዎች3
 የዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች /መካከለኛ ክብደት ያላቸው5
 የሥጋ ዝርያ እናቲት ዶሮዎች /እናት ዶሮ4

ተደራርቢ ጐጆዎች (Cage System)

ተደራርቢ የዶሮ እርባታ ጐጆዎች በብዛት ጥቅም ላይ የሚውለው በአደጉ የዓለማችን ክፍሎች ሲሆን በጣም ውጤታማ የሆነ የእንቁላል ዶሮዎች የሚረቡበት ነው፡፡ ምክንየቱም ዶሮዎች ወዲያ ወዲህ በማለት ጉልበት ስለማያባክኑ በቀን 5 ግራም/በዶሮ ዝቅ ያለ ይመገባሉ፤ ዕንቁላል ለመሰብሰብ፣ ውሀ ምግብ ለመስጠት፣ ኩስ ለመስብሰብ አውቆማቲክ በሆነ መልኩ መሰብሰብ ይቻላል፡፡ዶሮዎች ከራሳቸው ኩስ ጋር የመገናኘት እድል ስለሌላቸው የጥገኛ ተዋስያን እና የኮክሲድዮሲሳ ችግር አይኖርም፡፡ በአብዛኛው ለእንቁላል ዶሮዎች የሚመች ሲሆን ለስጋ እና ለወላድ ዶሮዎችም መስራት ይቻላል፡፡ የኬጅ እርባታ ወሳኝ የሚሆነው ጉልበት፣ ጉዝጓዝ ውድ ሲሆን፤ የመሬት እጥረት ሲኖር፣ የበሽታ ስጋት ሲኖር፣ ለረጅም ጊዜ ምርት ላይ የሚቆይ ከሆነ የአየር ንብረቱ ቀዝቃዛ ወይም እርጥብ ሲሆን ነው፡፡

የሀገራችን የኬጅ እርባታ ዓይነት ዶሮዎቹ ተደራራቢ በሆነና እርስ በርሳቸው በተያያዙ ትንንሽ ጐጆዎች ውስጥ እንዲኖሩ ተደርጎ ከጐጆዎች ጋር የተያያዘ የውሃና የመኖ ማቅረቢያ እንዲሁም ዶሮዎቹ እዚያው ጐጆው ውስጥ እንቁላል ከጣሉ በኋላ እንቁላል ከጐጆው ውስጥ ተንሸራትቶ በመውጣት ዶሮዎቹ በማይደርሱበት መልክ የሚከማችበት ሥፍራ ተደርጎ ይሰራል፡፡ የዶሮዎቹ ኩስ መቀበያ ከያንዳንዱ ደረጃ ሥር ይኖራል፡፡ የተደራራቢ ጐጆዎቹ ብዛት እንደቤቱ ትልቅነትና ለአየር እንቅስቃሴ ባለው አመቺነት ይወሰናል፡፡ ይህ ዓይነቱ ዶሮዎችን የማርቢያ ዘዴ በአብዛኛው የቦታ ጥበት ባለበት ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የጉልበት ወጪን የሚቀንስ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ የመሥሪያ ወጪው ወለል ላይ ከማርባት ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ ነው፡፡ የውሃና የመኖ አቅርቦት ኩስ የማስወገድ እንቁላልን ወደ ማከማቻ የማድረስ ሥራ እንደሚመረጠው ቴክኖሎጂ በሰው ኃይል፣ በከፊል አውቶማቲክና በሙሉ አውቶማቲክ ሊካሄድ ይችላል፡፡ በዚህ አሠራር ዶሮዎቹ ብዙ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ስለማይችሉ የሚመገቡት መኖ በአብዛኛ ለምርት ተግባር ይውላል፡፡

ለሥራው ሊመደብ በሚችል የገንዘብ መጠንና ለርባታው ካለው የመሬት መጠን ላይ ተመስርቶ አንደኛውን አማራጭ መውሰድ ይቻላል፡፡ በሁለቱም ዓይነት ቤቶች የሚካሄዱ ዘመናዊ ዶሮ እርባታዎች በተለይ ከተማና ከተማ ዙሪያ አካባቢው ይገኛሉ፡፡

አረባብና አያያዝ ዘዴ (husbandry and management System)

  • ቤቱ አዲስ ከሆነ መፀዳት እና መታጠብ አለበት፣
  • ቤቱ ከዚህ በፊት ግልጋሎት የሰጠ ከሆነ ግን ጉዝጓዙ ተጠርጎ ወጥቶ ከዶሮዎች ቤት 300 ሜ. ያህል ርቆ መጣል አለበት፣
  • ግድግዳዎች ወለሎችና ቁሣቁሶች በደንብ መፅዳት አለባቸው፣
  • ከ 6 እስከ 12 ሳ.ሜ. ጥልቀት ያለው ጉዝጓዝ እንደ አስፈላጊነቱ መጎዝጎዝ አለበት፣ በዶሮ ቤት ውስጥ የተጎዘጎዘው ጉዝጓዘዝ ዶሮዎቹ እስከሚወጡ ድረስ ጉዝጓዙ ለፀረ-ተዋስያን መራቢያ ምቹ ሁኔታን እንዳይፈጥር ደሮዎቹ እዛው እያሉ ጉዝጓዙን ማገላበጥ ያስፈልጋል፣
  • መጀመሪያ የተጠቀምንበትን ጉዝጓዙ በፍፁም ደግመን መጠቀም የለብንም፣
  • የውሃ መጠጫዎችን አለማፍሰሳቸውን ማረጋገጥ፣
  • የዶሮ መጠጫዎች በየቀኑ ጥዋትና ማታ መፅዳት አለበት፣
  • የዶሮ መመገብያ በሳምንት አንድ ጊዜ መታጠብ አለበት፣
  • የዶሮዎች መጠጫዎችና መመገብያችን በየጊዜዉ ማጽዳት በሽታን ለመከላከል ይረዳል፣
  • መመገቢያና መጠጫዎችም ዶሮዎች ከመግባታቸው በፊት መሞላት አለባቸው፣

የብርሃን ሁኔታ

ቄቦች ዕንቁላል መጣል ከመጀመራቸው በፊት የሚያገኙት የብርሃን መጠን ቀስ በቀስ እየጨመረ መሄድ አለበት፡፡ ዕንቁላል በሚጥሉበት ጊዜ በሙሉ ከ16 እስከ 18 ሰዓታት ብርሃን ሊያገኙ ይገባል፡፡

ምርታማ ያልሆኑ ዶሮዎችን ማስወገድ

  • የቅርብ ክትትልና አካላዊ ዕይታ በማድረግ የምርታማነት ባህሪ መገለጫ የሆኑ ባህሪያትን በመመልከት ምርታማ ያልሆኑ (እንቁላል የማይጥሉ) ዶሮዎችን ከእርባታ ለይቶ የማስወገድ ሥራ በቋሚነት መካሄድ አለበት፡፡ እንቁላል እንደማይጥሉ የተለዩ ዶሮዎች ጤነኛ ከሆኑ ለእርድ ማዋል ይቻላል፡፡
    • ምርታማ ያልሆኑት ዶሮዎችን ማስወገድ (የመኖ ወጪ ይቀንሳል፣ የእንቁላል ምርት ይጨምራል፣ ለጤናማ ዶሮዎች ቦታ ያስገኛል እና ለጤናማ ዶሮዎች ቦታ ያስገኛል)፡፡

መንቆር ቆረጣ (Debaking)

ዶሮዎች በማንኛውም ዕድሜ በብዛት በአንድ ቤት ዉስጥ በሚረቡበት ወቅት እርስ በርስ የመበላላት አዝማሚያ ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ይህን ለመከላከል በብዙ የእንቁላል ዝርያ ዶሮ እርባታዎች በቄብነታቸው መንቆራቸውን ማሳጠር የተለመደ ተግባር ነው፡፡ የመንቁር ቆረጣ ተግባር ዶሮዎች ካደጉና እንቁላል መጣል ከጀመሩ በኃላ ከሆነ ግን ጫና ዉስጥ ስለሚገቡና እንቁላል መጣል ስለሚያቆሙ መንቁራቸዉ እንዲቆረጥ አይመከርም፡፡ የዶሮዎች መንቁር የመቁረጡ ተግባር የሚከናወነዉ ለዚህ በተሠራ መቁረጫ ይሆናል፡፡

  • የታዳጊዎች ክብደት ክትትል

የታዳጊ ዶሮዎችን ክብደት በተለያየ ዕድሜ ለዝርያው ከወጣው ደረጃ ጋር በማወዳደር ተፈላጊ ዕድገት ከሌለ አስፈላጊ የእርምት እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ ያሉትን ዶሮች በሙሉ መመዘን አስቸጋሪና ዶሮቹንም መረበሽ ስለሚሆን በየ15 ቀናት ልዩነት ከቤቱ ውስጥ የተለያየ አካባቢ ከጠቅላላው የዶሮዎች ቁጥር 5% ያህል የሚሆኑትን ወስዶ በመመዘን ስለአጠቃላይ ሁኔታው ግምት መውሰድ ይቻላል፡፡

  • የማሳደጊያና የእንቁላል መጣያ ቤቶች የተለያዩ ከሆኑ ቄቦች ከ16 እስከ 21 ሣምንት ባሉት ዕድሜ ዉሰጥ ወደ እንቁላል መጣያ ቤት ሊዘዋወሩ ይችላሉ፡፡ ይህ አዲሱን ሁኔታ እንዲለማመዱ ይጠቅማል፡፡ ዶሮዎቹ እንቁላል መጣል ከሚጀምሩበት ወቅት ጥቂት ቀደም ብሎ መረጣ ማካሄድ ጥሩ ነው፡፡ ምርታማ የማይሆኑ የተለያየ ችግር ያለባቸው ዶሮዎችን ያለምንም ማመንታት ማስወገድ ትርፋማነትን ያሻሽላል፡፡

የቦታ ስፋት ፍላጐት

ይህ እንደዝርያው የሚለያይ ቢሆንም ለእንቁላል ጣይ ዶሮዎች በመሬት ላይ ለሚካሄድ እርባታ በአማካይ ለስድስት ዶሮዎች አንድ ካሬ ሜትር ቦታ በቂ ነው፡፡ በዶሮ ቤት ውስጥ ያለውን የአየር እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ መሣሪያ እስከሌለ ድረስ በአንድ ቤት ውስጥ አንድ የእንቁላል ዶሮ ማራቢያ ቤት ስፋቱ 12 ሜትር፣ርዝመቱ 20 ሜትር ታሳቢ ተደረጎ ከተሰራ ጠቅላላ ስፋቱ 240 ካሬ ሜትር 1440 የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ይይዛል፡፡ ነገር ግን አንድ ረድፍ (Block) የዶሮ ቤት ሲገነባ ስፋቱ ከ240 ካሬ ሜ. በላይ የሚሆን ከሆነ የአየር ዝውውርን ይገታል፡፡

ሰንጠረዝ 1. የቄብና የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የቦታ ፍላጎት

ተራ ቁጥርየዶሮ ዓይነት  ብዛት በካሬ ሜትር  
 የዕንቁላል ዝርያ ቄቦች ከ8 እስከ 18 ሳምንተ ዕድሜ8-12
 የዕንቁላል ጣይ5-7
  • ዕንቁላል መጣያ ሳጥን/egg laying nest

በዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቤት ውስጥ በቂ ዕንቁላል መጣያ ሳጥን መኖር አለበት፡፡ አንድ ዕንቁላል መጣያ ሳጥን ስፋቱ 30X30X35 ሣ.ሜ. የሆነ 5-6 ዶሮች ሂሣብ መዘጋጀት አለበት፡፡ አመቺ የሆነ ጉዝጓዝ በውስጡ መደረግ አለበት፡፡

  1. ፓኬጁ ስርጭትና ስልትየሥርጭት አካባቢ

ይህ ፓኬጅ የምርት ግብዓት /በተለይ መኖ/ እንዲሁም ከተሞችና በከተማ ዙሪያ ባሉት እንዲሁም የመሰረተ ልማት በተመቻቸባቸው አካባቢያቸው የሚካሄድ ነው፡፡

  1. ሊገኝ የሚችል ምርት

ከአንድ የእንቁላል ጣይ ዶሮ በዓመት 280 እና ከዚያ በላይ (እንደዝርያውና አያያዙ) እንቁላል ማግኘት ይቻላል፡፡ ከምርት በኋላ በህይወት ያሉት ዶሮዎች ለሥጋ ይውላሉ፡፡ ለመሬት ማዳበርና ለከብቶች/በጐች በመኖነት ሊያገለግል የሚችል ከ1000 ዶሮዎች 30 ኩንታል ከዶሮ ኩስ ጋር የተብላላ ጉዝጓዝ (poultry litter) ማግኘት ይቻላል ተብሎ ይታሰባል፡፡

  1. ብድር  

አርቢዎች የራሳቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ ይጠበቃል፡፡ አቅማቸው የማይችል ከሆነ ግን እንደ ሁኔታው የፋይናስና የብድር አቅርቦትን በተመለከተ በአካባቢው ባሉ የፋይናንስ ተቋማት የሚመቻች ይሆናል፡፡ ይህም በአነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ በከተሞችና በገጠር አካባቢ ለሚደራጁ ሴቶችና ወጣቶች የቦታ አቅርቦትን በተመለከተ በአካባቢው መስተዳድር የሚመቻች ሲሆን ከተማ መስተዳድሩ ለዶሮ እርባታ የሚያዘጋጃቸው ሼዶች ለዶሮዎች አመቺ እንዲሆን ከእንስሳት እርባታ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

የምርት ትግበራ እንቅስቃሴ ይዘት

4.3.     የአዋጭነት ስሌት ለእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ

የአዋጭነት ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖረው ግብዓት ወጪና የምርት መሸጫ ዋጋ ላይ ተመሥርቶ የሚለዋወጥ ቢሆንም በአማካይ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ እንደሚከተለው ተሰልቷል፡፡

የግብዓት ፍላጐት በምሳሌነት ለአነስተኛ 500 የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ለእንቁላል ምርት የቀረበ

ተ.ቁ    የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ )ካ.ሜ1005000 
2ማግለያካ.ሜ45000 
3የዕንቁላል መጣያቁጥር100200 
4የዕንቁላል መደርደሪያ ትሪቁጥር10050 
5መጠጫቁጥር20260 
6መመገቢያቁጥር20260 
7አካፋቁጥር1170 
8ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120 
9የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊትር)ቁጥር14500 
10የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር2600 
13አምፑል (60W)ቁጥር550 
14መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11000 
15የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር53200 
16የእጅ ጋሪቁጥር1      3500 
16ቄቦችቁጥር500200 
17መኖኪ.ግ24,82539 
19ክትባት/ቄብቁጥር5004 
20 መድሃኒትና ቫይታሚንቁጥር50010 
21ጉዝጓዝኩ/ል30100 
22ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፌክታንት)ሊትር6150 
23የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪወር192500 
24መዝገብቁጥር1120 
25ድምር    

ለአነስተኛ (500) የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ለእንቁላል ምርት የቀረበ የአዋጭነት ስሌት

ሰንጠረዥ 1 የቋሚ እቃዎች ወጪ

ተ.ቁ    የግብዓት አይነትመለኪያ ብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ )ካ.ሜ1005000500,000
2ማግለያካ.ሜ4500020,000
3የዕንቁላል መደርደሪያ ትሪቁጥር100505,000
4መጠጫቁጥር10026026,000
5መመገቢያቁጥር202605,200
6አካፋቁጥር201703,400
7ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120120
8የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊትር)ቁጥር145004,500
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር1600600
10አምፑል (60W)ቁጥር250100
11መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር510005,000
12የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር132003,200
13የእጅ ጋሪቁጥር5350017,500
  ድምር   590,620

ሰንጠረዥ 2 የቋሚ እቃ የአገልግሎት ዘመንና ተቀናናሽ ወጪ

ተ/ቁየግብዓት አይነትመለኪያጠ/ዋጋየአገልግሎት ዘመንየ1 ዓመት ተቀናናሽ ወጪየ1 ምርት ዘመን ተቀናናሽ ወጪ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ ፤ካ.ሜ500,0001533,33338,461.54
2ማግለያካ.ሜ20,000151,3331,538.46
3የዕንቁላል መደርደሪያ ትሪቁጥር5,00051,0001,153.85
4መጠጫቁጥር26,00055,2006,000.00
5መመገቢያቁጥር5,20031,7332,000.00
6አካፋቁጥር34005680784.62
7ሬክ/መቧጠጫቁጥር12052427.69
8የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊትር)ቁጥር4,50010450519.23
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር6002300346.15
10አምፑል (60W)ቁጥር1001100115.38
11መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር5,00010500576.92
12የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር3,20010320369.23
13የእጅ ጋሪቁጥር17,500101,7502,019.23
 ድምር   46,724.0053,912.31

ሠንጠረዥ3 የተንቀሳቃሽ ዕቃዎች ወጪ

ተ.ቁ    የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋየ1 ምርት ዘመን  ወጪ
1ቄቦችቁጥር500200100,000
2መኖ (Feed)ኪ.ግ24,82539968,175
3ክትባት/ቄብዶዝ5000.5250
4 መድሃኒትና ቫይታሚንቪያል/ሳቸት500200100,000
5ጉዝጓዝኩ/ል301003,000
6ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፌክታንት)ሊትር6150900
7የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪወር195,000
8መዝገብቁጥር1120120
 ድምር   1,177,445
 የአገልግሎት ዘመን ተቀናናሽ ወጪ   53,912.31
 ጠቅላላ ድምር   1,231,357.31
 መጠባበቂያ 5%            61,567.87
 ጠቅላላ ወጪ   1,292,925.17

ሰንጠረዥ 4 የገቢ ስሌት

ተ.ቁየገቢ ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋየ1 ምርት ዘመን የገቢ ስሌት
1ዕንቁላል ምርት ያቆሙ ዶሮዎች ሽያጭቁጥር475350166,250
2የዕንቁላል ሽያጭቁጥር133,000101,330,000
3ከዶሮ ኩስ ሽያጭኩ/ል302006,000
4የገቢ ድምር1,502,250
5የወጪ ድምርብር  1,292,925
6ያልተጣራ ትርፍብር  209,325

ማጠቃለያ፡-

  • በግል/በቡድን ተደራጀተው የእንቁላል ምርት ላይ የተሰማሩ አርቢዎች በአንድ የምርት ዘመን ማለትም በ 60 ሳምንት ውስጥ የተጣራ ገቢ የሚያገኘው/ኙት 209,325 ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡
  • በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡

ታሳቢዎች፡-

  • የሞት መጠን 5% ታሳቢ ተወስዷል ስለሆነም 500X5% = 475 ቄቦች ያድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • መጠባበቂያ 5% ታሳቢ ተወስዷል፡፡

ለመካከለኛ (1000) የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ለእንቁላል ምርት የቀረበ የአዋጭነት ስሌት

ተ.ቁ    የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ ፤ካ.ሜ2005000
2ማግለያካ.ሜ85000
3የዕንቁላል መደርደሪያ ትሪቁጥር20050
4መጠጫቁጥር40260
5መመገቢያቁጥር40260
6አካፋቁጥር2170
7ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120
8የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊትር)ቁጥር14500
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር2600
10አምፑል (60W)ቁጥር1050
11መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11000
12የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር103200
13የእጅ ጋሪቁጥር13500
14ቄቦችቁጥር1000          200
15መኖ (Feed)ኪ.ግ4965039
16ክትባት/ቄብዶዝ40000.50
17 መድሃኒትና ቫይታሚንሳቸት/ቪያል50200
18ጉዝጓዝኩ/ል60100
19ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፌክታንት)ሊትር12150
20የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪወር0
21መዝገብቁጥር2120
 ድምር   

ሰንጠረዥ 1 የቋሚ እቃዎች ወጪ

ተ.ቁ    የግብዓት አይነትመለኪያ ብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ ፤ካ.ሜ2005000 1,000,000
2ማግለያካ.ሜ85000 40,000
3የዕንቁላል መደርደሪያ ትሪቁጥር20050 10,000
4መጠጫቁጥር40260 10,400
5መመገቢያቁጥር40260 10,400
6አካፋቁጥር2170 340
7ሬክ/መቧጠጫቁጥር1120 120
8የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊትር)ቁጥር14500 4,500
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር2600 1,200
10አምፑል (60W)ቁጥር1050 500
11መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር11000 1,000
12የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር103200 32,000
13የእጅ ጋሪቁጥር13500 3,500
 ድምር   1,113,960

ሰንጠረዥ 2 የቋሚ እቃ የአገልግሎት ዘመንና ተቀናናሽ ወጪ

ተ/ቁየግብዓት አይነትመለኪያጠ/ዋጋየአገልግሎት ዘመንየ1 ዓመት ተቀናናሽ ወጪየ1 ምርት ዘመን ተቀናናሽ ወጪ
1የእርባታ ቤት (የጥበቃ  ፤ የማከማቻ ፤ካ.ሜ 1,000,0001566,666.67 76,923.08
2ማግለያካ.ሜ 40,00015 2,666.67 3,076.92
3የዕንቁላል መደርደሪያ ትሪቁጥር 10,0005 2,000.00 2,307.69
4መጠጫቁጥር 10,4005 2,080.00 2,400.00
5መመገቢያቁጥር 10,4003 3,466.67 4,000.00
6አካፋቁጥር 3405 68.00 78.46
7ሬክ/መቧጠጫቁጥር 1205 24.00 27.69
8የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (ባለ1000 ሊትር)ቁጥር 4,50010 450.00 519.23
9የእርባታ ትጥቅ (አልባሳት)ቁጥር 1,2002 600.00 692.31
10አምፑል (60W)ቁጥር 5001 500.00 576.92
11መርጫ መሣሪያ (ናፕ ሳክ ሰፕሬየር)ቁጥር 1,00010 100.00 115.38
12የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (Crate)ቁጥር 32,00010 3,200.00 3,692.31
13የእጅ ጋሪቁጥር 3,50010 350.00 403.85
ድምር  1,113,960 82,172.0194,813.84
ሰንጠረዥ 3 የተንቀሳቃሽ እቃዎች ወጪ 
ተ.ቁ    የግብዓት ዓይነትመለኪያብዛትየአንዱ ዋጋየ1 ምርት ዘመን  ወጪ
1ቄቦችቁጥር1000200        200,000
2መኖ (Feed)ኪ.ግ4965039 1,936,350
3ክትባት/ቄብዶዝ4,0000.50 2,000
4 መድሃኒትና ቫይታሚንቪያል/ሳቸት50200 10,000
5ጉዝጓዝኩ/ል60100 6,000
6ጸረ-ተባይ ኬሚካሎች (ዲስ ኢንፌክታንት)ሊትር12150 1,800
7የኤሌክትሪክና ዉሃ ወጪወር010,000
8መዝገብቁጥር2120 240
ድምር   2,166,390
የአገልግሎት ዘመን ተቀናናሽ ወጪ   94,813.84 
 ጠቅላላ ድምር   2,261,203.84
 መጠባበቂያ 5%    113,060.2
ጠቅላላ ወጪ    2,374,264.03

ሰንጠረዥ 4 የገቢ ስሌት

ተ.ቁየገቢ ዓይነትመለኪያብዛትያንዱ ዋጋየ1 ምርት ዘመን የገቢ ስሌት
1ዕንቁላል ምርት ያቆሙ ዶሮዎች ሽያጭቁጥር950350332,500
2የዕንቁላል ሽያጭቁጥር266,000102,660,000
3ከዶሮ ኩስ ሽያጭኩ/ል6020012,000
4የገቢ ድምር3,004,500
5የወጪ ድምርብር  2,374,264.03
6ያልተጣራ ትርፍብር  630,236

ማጠቃለያ፡-

  • በግል/በቡድን ተደራጀተው የእንቁላል ምርት ላይ የተሰማሩ አርቢዎች በአንድ የምርት ዘመን ማለትም በ 60 ሳምንት ውስጥ የተጣራ ገቢ የሚያገኘው/ኙት  630,236 ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡
  • በወጪ ገቢ ስሌት ላይ ታክስ አልተካተተም፡፡

ታሳቢዎች፡-

  • የሞት መጠን 5% ታሳቢ ተወስዷል ስለሆነም 1000X5% = 950 ቄቦች ያድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • መጠባበቂያ 5% ታሳቢ ተወስዷል፡፡

ሠንጠረዠ5. አማራጭ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖ ቀመሮች

የግብዓት ዓይነትየጫጩት አማራጭ ቀመሮችየቄብ ዶሮዎች አማራጭ ቀመሮችየዕቁላል ጣይ ዶሮዎች አማራጭ ቀመሮች
123123123
በቆሎ53.745.061.061.057.859.360.063.057.0
የአኩሪ አተር ፋጉሎ18.0 22.0 18.0 18.020.0 
የለውዝ ፋጉሎ6.0    8.0   
የተቆላ አኩሪ አተር   22.0 10.0   
የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ5.09.0       
የሰሊጥ ፋጉሎ 16.0       
የሱፍ ፋጉሎ    10.0    
የኑግ ፋጉሎ     16.0  18.0
አልፋ አልፋ  5.05.0     
ሞላሰስ 0.52.0     0.5
የተፈጨ አሳ 7.0 3.0     
የተፈጨ አጥንት3.01.53.02.0  6.02.05.0
የኖራ ድንጋይ 1.50.50.5  6.66.03.0
የተፈጨ ሥጋ       4.5 
የተፈጨ ሥጋና አጥንት    5.05.5   
ፉሩሽኬሎ/ፊኖ13.018.05.05.08.0 8.03.015.0
L-ላይሲን0.40.30.30.30.40.40.30.30.3
DL-ሜታዪኒን0.20.20.20.20.10.10.10.20.2
ጨው0.20.50.50.50.20.20.50.50.5
የቫይታሚንና ንዑስ  ማዕድናት ቅይጥ0.50.50.50.50.50.50.50.50.5
ድምር100100100100100100   
የድብልቅ መኖው የሃይል ሰጪ ይዘት (ኪሎ ካሎሪ/ኪሎ ግራም መኖ)274426962764282028942854  2619  2765  2649
የድብልቅ መኖው የፕሮቲን ይዘት(%)20.3622.6919.041717.815.9816.6818.0115.69
የሃይል ሰጪ ንጥረ ምግብ ፍላጎት280027502750
የፕሮቲን ፍላጎት20%16%16.5%

5.   የተሻሻለ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

 

ጥምር ጠቀሜታ/የዕንቁላልና የሥጋ ምርት ፓኬጅ

የፓኬጁ ዓላማ

የዚህ ፓኬጅ አተገባበር የተመረጡ ጥምር ጠቀሜታ ያላቸዉ ዶሮዎች ላይ የተመሠረተና ከእያንዳንዷ ዶሮ የእንቁላልና ሥጋ ምርት በማምረት ለገበያ  ለማቅረብ  እና ስነ-ዓመጋገብ ለማሻሻል ያለመ ሥራ ሲሆን ዋናው ዓላማ መንግስት ለነደፈው ለሌማት ቱርፋት እና  ለአስር  ዓመት መሪ ዕቅድ  ግብ ለማሳካት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

በዚህም መሠረት ከዶሮ ሀብት ልማት ፓኬጆች አንዱና አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ጥምር ግብርና የሚያካሂደውን አርሶ አደር ከግምት ውስጥ ያስገባ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የተሻሻለ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ (Improved Family Poultry)

በዚህም መሠረት አንድ ፓኬጅ 25 ጥምር ጠቀሜታ ያላቸዉ (Dual Purpose) ቄብና ኮከኔዎችን ይይዛል፡፡ ከሁለቱ በአንዱ ስራ ላይ ብቻ ማተኮር ለፈለጉ 25 ቄቦችን በመያዝ እንቁላል ማምረት ወይንም 25 ኮክኔዎችን በመያዝ ለስጋ መሸጥ ይችላሉ፡፡

ይህ ፓኬጅ የእንቁላልና ሥጋ ምርት የሚሰጡ ዝርያ ዶሮዎች ላይ ተመሥርቶ በዋነኛነት የመብል እንቁላልና ሥጋ ለገበያ በማቅረብ የገቢ ምንጭ ለማስገኘትና የቤተሰብን የምግብ ፍላጎትን (በተለይም የፕሮቲን አቅርቦት) ለማሟላት የሚያስችል የአሰራር ሥልት ነው፡፡

5.1.     የተሻሻለ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ ማስፈጸሚያ ስልት

በዚህ ፓኬጅ እነዚህ ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው የዕንቁላልና የሥጋ ዶሮዎች በግል ወይም በማህበር በጫጩት ማሳደግ ከተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች/ ግለሰቦች እንዲሁም የግልና የመንግስት ማባዣ ማዕከላት ይገኛሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ በመሆኑም በዚህ ፓኬጅ አርቢው 45 ቀን የሞላቸውን 25 ቄብና ኮክኔዎች (50 በመቶ ወንድና 50 በመቶ ሴት እንደሚሆን ይጠበቃል) በመውሰድና አንድ ላይ በማሳደግ ኮክኔዎቹ እድሜያቸው ለጥቂ ሳይደርስ (ከ20 ሳምንት) በፊት ለስጋ አውጥቶ መሸጥና የቀሩትን 50 በመቶ ሴቶች ለእንቁላል በማስቀረት እንቁላል ማምረት ሲሆን፣ ከሁለቱ በአንዱ ማተኮር ለፈለጉ አርብቶ አደረሮች ደግሞ 25 ቄቦችን ብቻ በመውሰድ እንቁላል ማምረት ወይም በስጋ ምርት ላይ ማተኮር የፈለጉት ደግሞ  25 ኮክኔዎችን ብቻ በመውሰድ ለስጋ አሳድጎ በመሸጥ እንደሚከናውን ይጠበቃል፡፡

ሀ. ዝርያ

ጥምር(የእንቁላልና ሥጋ) ምርት የሚሰጡ ዝርያ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሚገኙትን ኮክኮክና ሳሶ ለዚህ እርባታ እንዲዉሉ በማድረግ አርቢዎች የዕንቁላልና የሥጋ ምርት እንዲያገኙና የቤተሰቡን የፕሮቲን ፍላጎት እንዲያሟሉ እንዲሁም ትርፍ ምርትን በመሸጥ የገቢ አቅማቸውን ለማሳደግ የተቀረጸ ፓኬጅ ነዉ፡፡

ለ. አመጋገብ፡-

የዶሮዎች አመጋገብ በአጠቃላይ በሦስት ይከፈላል ይህም የጫጩት መኖ  እድሜያቸው ከ0-8 ሳምንት እድሜ የሚመገቡት ሲሆን የቄብ መኖ/ ከ8-18 ሳምንት እድሜ የሚመገቡት ሲሆን ከ18 ሳምንት በኋላ ባለ እድሜያቸው የሚመገቡት መኖ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች መኖ ይባላል፡፡ በዚህም መሰረት ለእርባታ የምናመጣቸው የ45 ቀን ጫጩቶች ከቄብ መኖ ጀምረው በአግባቡ መመገብ እንዳለባቸው ይጠበቃል፡፡

የታዳጊ /ቄብ/ኮክኔ አመጋገብ

የቄብና ኮከኔ ዶሮዎች አመጋገብ ለቀጣዩ የእንቁላልና ሥጋ ምርት ውጤታማነት ወሳኝ ነው በመሆኑም በዚህ ወቅት ለአንድ ዶሮ በአማካይ በቀን 35 ግራም ታሳቢ ተደርጓል፡፡ ቄቦችና ኮከኔዎች ለዝርያቸው የሚመጥን ዕድገት ኖሯቸው በተገቢው ወቅት የዕንቁላልና ሥጋ ምርት መስጠት ተግባራቸውን መጀመር አለባቸው፡፡ ለእንቁላል ምርት የምናዘጋጃቸው ቄቦች በዚህ ዕድሜ ከጫጩትነት ጊዜ የፕሮቲን ፍላጐት ይቀንሳል፡፡ በዚህ ወቅት የፕሮቲን ፍላጐት ከ15-16% ይሆናል፡፡ ከዚህ የበለጠ የፕሮቲን አቅርቦት የመኖ ወጪን ከመጨመሩ በላይ ቄቦች ከሚፈለገው የዕድገት መጠን በላይ በማደግ የመራቢያ አካላቸዉ ሳይዳብር ዕንቁላል መጣል  እንዲጀምሩ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የዶሮቹን የምርት ዘመን ውጤታማነት ይቀንሰዋል፡፡ ኃይል ሰጪ ንጥረ ምግብን በተመለከተ በ14 ሣምንት ዕድሜ 2900 ኪሎ ካሎሪ በኪሎ መኖ ሲያስፈልግ ከ14-20 ሣምንት ባለው ዕድሜ ግን የስብ ክምችትን ለመከላከል 2700 መቀነስ ይኖርበታል፡፡ በተመሳሳይ ለስጋ ምርት አሳድገን የምናወጣቸው ዶሮዎች ለስጋ ዶሮዎች የተዘጋጀውን ቀመር በመጠቀም ለስጋ አድርሶ መሸጥ ያስፈልጋል፡፡

ጥምር ጠቀሜታ ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎች አመጋገብ

ቄብ ዶሮዎች ዕንቁላል መጣል ከሚጀምሩበት ጥቂት ቀደም ብሎ የመኖ ለውጥ ሂደት መጀመር አለበት፡፡ በዚህ ወቅት ከታዳጊዎች መኖ ወደ እንቁላል ጣይ መኖ ለውጥ ይደረጋል፡፡ የዕንቁላል ምርት ፍላጐትን ለማርካት የካልሲየም አቅርቦት መጨመር አለበት፡፡ ይህም በመኖ ውስጥ ከሚደባለቀው በተጨማሪ በተለየ መመገቢያም ከፍተኛ የካልሲየም ይዘት ያለው ያልደቀቀ በዛ ያለ ድንጋይ ለእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሊቀመጥላቸው ይገባል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ 2850 ኪሎ ካሎሪ በኪ.ግ. መኖ የኃይል ምንጭ ሊኖረው ይገባል፡፡ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የፕሮቲን ፍላጐት ከእንቁላል ምርት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእንቁላል መጣያ ወቅት ያለውን አማካይ ፍላጐት ለማርካት የእንቁላል ጣይ መኖ 16.5% ፕሮቲን ሊኖረው ይገባል፡፡

ከላይ የተዘረዘረውን የንጥረ መኖ (nutrient) ፍላጐት የሚያሟላ የተደባለቀ መኖ ከመኖ ማደራጃዎች መግዛት ወይም በአካባቢው ከሚገኙ ጥሬ ዕቃዎች በባለሙያ ድጋፍ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

ሐ. ጤና

ክትባት፡- በቄብነት ወደ እርባታው ከመግባታቸው በፊት የሚሰጡ ክትባቶች የወሰዱ መሆን አለባቸዉ፡፡ ወደ እርባታው ከገቡ በኋላ የፈንግል በሽታ ክትባት በየ2 ወሩ ላሶታ መከተብ አለባቸዉ፡፡

      የመከላከል እርምጃዎች

  • ዶሮዎችን በእድሜ ለይቶ ማርባት፡- የታመሙ ዶሮዎችን ከጤነኛው ለይቶ ማከም
  • ከበሽታ አስተላላፊዎች መጠበቅ (የሰራተኛ አልባሳትን ማዘጋጀት፣ ወደ እርባታው የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ የተለያዩ አውሬዎች በአካባቢው እንዳይኖሩ ማድረግ)
  •  የአካባቢውን ንፅህና መጠበቅ. ወዘተ

መ. መጠለያ

ለሥጋ ዶሮዎች ከተቀመጠው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቢሆንም ጥምር ጠቀሜታ ላላቸዉ ሮዎች የወለል ስፋት ፍላጐት ከፍ ያለ ነው፡፡  የመመገቢያ ፍላጐታቸው 1. ሣ.ሜ. ለ1ዶሮ ሲሆን የመጠጫ ፍላጐታቸው 2.5 ሣ.ሜ. ለ1 ዶሮ ነው፡፡ የዕንቁላል መጣያ ሳጥን (egg laying nest) መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የዕንቁላል መጣያዉ ልኬታ 30*30*35ሣ.ሜ ሲሆን ለአምስት ዶሮ አንድ ዕንቁላል መጣያ ያስፈልጋል፡፡

ሠ. አረባብና አያያዝ

ቄቦች ዕንቁላል መጣል ከመጀመራቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ጀምሮ የሚያገኙት ብርሃን መጠን ቀስ በቀስ እየጨመረ መሄድ አለበት፡፡ ዕንቁላል በሚጥሉበት ጊዜ በሙሉ ከ14 እስከ 16 ሰዓታት ብርሃን ሊያገኙ ይገባል፡፡ የቅርብ ክትትል በማድረግ ምርታማ ያልሆኑ ዶሮዎችን ለይቶ የማስወገድ ሥራ በቋሚነት መካሄድ አለበት፡፡ በተጨማሪም ዶሮዎች ሲሞቱ ወይም ማስወገድ ሲፈለግ ማቃጥል ወይም በጥልቅ ጉድጓድ መቅበር አስፈላጊ ነዉ፡፡

ሰ. የግብዓት ፍላጐት /ጥንቅር/

የግብዓት ዓይነቶችመለኪያብዛትምርመራ
ጥምር ጠቀሜታ ያላቸዉ ዝርያ ቄቦችቁጥር25 
የተመጣጠነ መኖኪ.ግ621 
ክትባት/ሕክምናዶዝ100 
መጠለያካ.ሜ4ከአከባቢ ቁሳቁስ
የዕንቁላል መጣያቁጥር1መጣያ ባለ 5 ክፍል 
መመገቢያቁጥር1 
መጠጫቁጥር1 
የዕንቁላል ማጓጓዣቁጥር1ከአካባቢ ቁሳቁስ/ዘንቢል
የዕንቁላል መሰብሰቢያቁጥር1 

         የቦታ ስፋት ፍላጐት

ይህ እንደ ዝርያው የሚለያይ ቢሆንም ጥምር ጠቀሜታ ላላቸዉ ዶሮዎች በመሬት ላይ ለሚካሄድ እርባታ በአማካይ ለሰባት ዶሮዎች አንድ ካሬ ሜትር ቦታ በቂ ነው፡፡

ሸ. ሊገኝ የሚችል ምርት

  • ከአንድ ጥምር ጠቀሜታ ካላቸዉ ዶሮዎች በዓመት በአማካይ 180 እንቁላል ማግኘት ይቻላል፡፡
  • ከአንድ የምርት ዘመን በኋላ በህይወት ያሉት ዶሮዎች  ለሥጋ ይውላሉ፡፡
  • በአንድ የምርት ዘመን (52 ሣምንት) በአማካይ 180 እንቁላል ከአንድ ዶሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
  • ለመሬት ማዳበርና ለከብቶች/በጐች በመኖነት ሊያገለግል የሚችል ከ100 ዶሮዎች 3 ኩንታል ከዶሮ ኩስ ጋር የተብላላ ጉዝጓዝ (poultry litter) ማግኘት ይቻላል፡፡

ቀ. የሥርጭት አካባቢ

ይህ ፓኬጅ ጥምር ግብርና በሚካሄድባቸዉ የገጠር ኣካባቢዎች መተግበር የሚችል ፓኬጅ ነው፡፡

5.2.     የአዋጭነት ስሌት የተሻሻለ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ

 

 የአዋጭነት ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖረው ግብዓት ወጪና የምርት መሸጫ ዋጋ ላይ ተመሥርቶ የሚለዋወጥ ቢሆንም በአማካይ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ እንደሚከተለው ተሰልቷል፡፡

ለተሸሻለ የቤተሰብ ዶሮ እርባታ ፓኬጅ የሚያስፈልጉ የግብዓት አይነቶቸና ዋጋቸው

የግብዓት ዓይነቶችመለኪያብዛትየአንድ ዋጋጠቅላላ ዋጋምርመራ
መጠለያካ.ሜ4875 3500
ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ቄቦች እና ኮከኔዎች     ቁጥር  251503750 
የዕንቁላል መጣያቁጥር4         0        ከአካባቢ ቁሳቁስ
ሜሽ ዋየር ለአጥርሜት.30   66.67 2000 
መኖኪ.ግ621       2515525ከአካባቢ ጥራጥሬ የሚዘጋጅ.
መመገቢያቁጥር1 0ከአካባቢ ቁሳቁስ
መጠጫቁጥር1 0ከአካባቢ ቁሳቁስ
ክትባትዶዝ1000.5050 
መዲሀንትና ቫይታሚንቭያል/ሳቸት25001000 
የዕንቁላል ማጓጓዣቁጥር1 0ከአካባቢ ቁሳቁስ
የዕንቁላል መሰብሰቢያቁጥር1 0ከአካባቢ ቁሳቁስ
የዶሮ ቆጥቁጥር1 0ከአካባቢ ቁሳቁስ
ጠቅላላ ዲምር   25,825 

የቋሚ እቃዎች ወጪ

ተ.ቁ   የግብዓት ዓይነት መለኪያብዛትየአንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
1መጠለያካ.ሜ48753500
2የዕንቁላል መጣያ ሳጥንቁጥር40
3ሜሽ ዋየር ለአጥርሜ.3066.672000
4መመገቢያቁጥር10
5መጠጫቁጥር10
6የዕንቁላል ማጓጓዣቁጥር10
7የዕንቁላል መሰብሰቢያቁጥር10
8የዶሮ ቆጥቁጥር10
 ድምር   5,500

ሰንጠረዥ 2 የቋሚ እቃ የአገልግሎት ዘመንና ተቀናናሽ ወጪ

  የግብዓት ዓይነቶች  መለኪያ  ጠቅላላ ዋጋየአገልግሎት ጊዜ የአንድ አመት ተቀናናሽየአንድ ምርት ዘመን ተቀናናሽ   ምርመራ
መጠለያካ.ሜ350010 350404 
የዕንቁላል መጣያ ሳጥንቁጥር0  00        ከአከባብ ቁሳቁስ
ሜሽ ዋየር ለአጥርሜ.20004 500577 
መመገቢያቁጥር0  00ከአካባቢ ቁሳቁስ
መጠጫቁጥር0  00ከአካባቢ ቁሳቁስ
የዕንቁላል ማጓጓዣቁጥር0  00ከአካባቢ ቁሳቁስ
የዕንቁላል መሰብሰቢያቁጥር0  00 ከአከባብ ቁሳቁስ
የዶሮ ቆጥቁጥር0  00ከአካባቢ ቁሳቁስ
ጠቅላላ ዲምር 5,500  850981 

የተንቀሳቃሽ ዕቃዎች ወጪ

  የግብዓት ዓይነቶች  መለኪያ    ብዛት  የአንዱ ዋጋ  የአንድ ምርት ዘመን ወጪየአንድ አመት ተቀናናሽ  ምርመራ
ቄብና ኮከኔዎች     ቁጥር25150        3750  
  መኖ  ኪ.ግ6212515525      ከአከባብ ጥራጥሬ                                    
  ክትባትዶዝ1000.50             50  
መድሃንትና ቫይታሚንቭያል/ሳቸት25001000  
የአገልግሎት ተቀናናሽቁጥር  981850 
ዲምር   21,306850 

ትርፍና ኪሳራ

የግብዓት አይነቶች መለኪያ64 ሣምንት (አንድ የምርት ወቅት)ምርመራ
ብዛትያንዱ ዋጋጠቅላላ ዋጋ
ዕንቁላል ምርት ያቆሙ ዶሮዎች ሽያጭቁጥር23                     400       9200 
የዕንቁላል ሽያጭቁጥር4140                        10      41400 
ጠቅላላ ገቢ   50600 
ጠቅላላ ወጪብር           21,306 
ያልተጣራ ትርፍብር  29,294 


ሰንጠረዝ 2. ¾”lLM ´`Á Êa T^ß ¾S Ø”pa(%)

የመኖ ጥሬ ዕቃ ጫጩት (0-8 ሣምንት ዕድሜ)ታዳጋ (8-18 ሣምንት)እንቁላል ጣይ (-18 ሣምንት)
12345678912345123456789
የተከካ በቆሎ5050503630254744304842504232403740454840253651
ፉሩሽኬሎ 25292918192791020231016221832232610142010
የተፈጨ ሥጋና አጥንት 444610107559585.5107
የኑግ ፋጉሎ 2035151324213533373018.51815112010
የጐመን ዘር ፋጉሎ 16
የጥጥ ፍሬ ፋጉሎ 16
ጨው<0.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.5
የቪታሚንና ማዕድን ድብልቅ*0.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.50.5
የተከካ የኖራ ድንጋይ 112211213.54.53333
የተፈጨ አጥንት 322122453.53.5
ማሽላ 2523142153016
የቢራ አተላ 1515
የቢራ ብቅል ተረፈ ምርት 10
አልፋ አልፋ ቅጠል 55555544
የለውዝ ፋጉሎ 2020151510
የተፈጨ ሥጋ 44443.54.5
የተፈጨ ዓሣ 333333
ገብስ10101010

* አምራቹ ድርጅት በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የሚጨመረ መጠን ሊለያይ ይችላል፡፡

ፓኬጅ ማስፈጸሚያ ስልቶች

. ብድር

  • የብድር አቅርቦትን በተመለከተ አርቢዎች የራሳቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን አቅማቸው የማይችል ጫጩት አሳዳጊዎች እንደሁኔታው በአካባቢው ባሉ የፋይናንስ ተቋማት የሚመቻች ይሆናል፡፡ ይህም በአነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

Tags:

59 Responses

  1. naturally like your web site however you need to take a look at the spelling on several of your posts. A number of them are rife with spelling problems and I find it very bothersome to tell the truth on the other hand I will surely come again again.

  2. This is really interesting, You’re a very skilled blogger. I’ve joined your feed and look forward to seeking more of your magnificent post. Also, I’ve shared your site in my social networks!

  3. You’re so awesome! I don’t believe I have read a single thing like that before. So great to find someone with some original thoughts on this topic. Really.. thank you for starting this up. This website is something that is needed on the internet, someone with a little originality!

  4. I’m often to blogging and i really appreciate your content. The article has actually peaks my interest. I’m going to bookmark your web site and maintain checking for brand spanking new information.

  5. Ufabet เว็บพนันออนไลน์ที่มีระบบการเดิมพันที่ปลอดภัย: ปลอดภัย มั่นใจได้ เงินไม่หาย

  6. อัตราต่อรองดีที่สุด: อัตราต่อรองดีที่สุด ให้ราคาสูง

  7. วิเคราะห์เกม: ดูบาสสด นำเสนอวิเคราะห์เกมบาสเก็ตบอลจากกูรูผู้เชี่ยวชาญ ช่วยให้นักดูบอลติดตามข่าวสาร วิเคราะห์เกมได้อย่างแม่นยำ

  8. มีกลุ่มนักเดิมพัน: กลุ่มนักเดิมพัน ให้คำปรึกษา แชร์ประสบการณ์

  9. เล่นได้อย่างเพลิดเพลิน: เล่นเพลินๆ แก้เบื่อ ผ่อนคลายความเครียด

  10. Ufabet เว็บพนันออนไลน์ที่เล่นง่าย: รองรับการเล่นผ่านมือถือ เล่นง่าย สะดวก ทุกที่ทุกเวลา เล่นได้ทุกระบบปฏิบัติการ เล่นได้บนทุกอุปกรณ์

  11. เล่นได้โดยไม่ต้องติดตั้งโปรแกรม: เล่นได้โดยไม่ต้องติดตั้งโปรแกรม สะดวก รวดเร็ว

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *